COVID19

COVID19

REPORTER ANTENEH

June 11, 2020

በድንገት ህይወታቸው የሚያልፉ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ሲደረግላቸው በውስጣቸው ቫይረሱ እንዳለባቸው ይገለፃል ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የበርካታ ሰዎች ጥያቄ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡በዚህም ዙሪያ በኮቪድ-19 አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የክሊኒካል ኬዝ-ቲም ዩኒት አስተባባሪ ዶክተር ሚኪያስ ተፈሪ ይህ ሊሆንበት የሚችልባቸውን ምክንያቶች ሲዘረዝሩ፤ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ በውስጣቸው እያለባቸው የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነታቸው ዝቅተኛ ሆኖ ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል፤ ሌሎቹ የኮሮና ቫይረስ በውስጣቸው ኖሮባቸው ምልክቶችን ሳያሳዩ በድንገት በሌሎች የጤና ችግሮች ምክንያት ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ፣ በምርመራ ወቅት የሚወሰደው ናሙና እስኪደርስ ድረስ ቫይረሱ እንዳለባቸው ሳይታወቅ ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ከዚህ በተጨማሪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድንገተኛ በሆነ ህመም መባባስ ምክንያት በበሽታው ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ብለዋል፡፡ 


በጤና ሚኒስቴር በተላለፈው መሰረት ህይወቱ የሚያልፍ ማንኛውም ሰው አስክሬኑ እንዲመረመር እየተደረገ ይገኛል፡፡የአስክሬን ምርመራ በሚደረግበት ግዜ የኮሮና ቫይረስ እንዳለበት ከታወቀ ወረርሽኙ በቀላሉ ወደ ህበረተሰቡ እንዳይዛመት ያግዛል፡፡በአስክሬን እጥበት፤በግነዛ፤በስረዓተ-ቀብር እና በመሳሰሉት ስራዎች ላይ በቀጥታ ተሳታፊ የሚሆኑ ሰዎች በቀላሉ በቫይረሱ የመያዝ እድል ይኖራቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ደግሞ በቀጥታ ከማሕበረሰቡ ጋር ስለሚቀላቀሉ ወረርሽኙ የመስፋፋት እድሉን ያባብሰዋል ብለዋል ዶክተር ሚኪያስ ፡፡


ይህ መደረጉ በቤት ለቤት እና በጤና ተቋማት በሚደረገው ምርመራና ልየታ ወቅት ምልክቱን ስላላሳዩ ያላገኘናቸውን ሰዎችም ጭምር ወረርሽኙ ከዚህም በባሰ ሁኔታ ሳይሰፋ ለመለየት እያገዘ ይገኛል ፡፡ 


ስለዚህ አሁንም ህብረተሰቡ እጁን በንፁህ ውሃና ሳሙና በተደጋጋሚ በመታጠብ፤የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ፤ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለንን አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም ግዴታ ካልሆነ በስተቀር ከቤት ባለመውጣት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመቆጠጠር ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅኦ መወጣት ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 


በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ከምልክቶቹ አንዱን ቢሰማዎት በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

https://t.me//ethio_mereja

ይቀላቀሉን።

Report Page