#covid19

#covid19


በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ተጨናንቆ ከሚኖርባቸው አካባቢዎች በአንዱ ፣ አብነት አካካቢ፣ የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ሲባል ሙሉ በሙሉ አንድ መንደር በእንቅስቃሴ ውጭ ተደርጎ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ መከልከሉን ዋዜማ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በልደታ ክፍለከተማ አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወረዳ 3 ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው 32 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ግለሰቡ በተጎዳኝ ህመሞች ለረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው ህይወታቸው አልፎል፡፡

ቀድሞ የተወሰደው ናሙና ሟቹ ግለሰብ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በማሳየቱ ከሳቸው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ላይ ምርመራና ክትትል ተደርጎ 32 ስዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከባለሙያዎች ተሰምቷል።

ይህንን ተከትሎም በወረዳው (አብነት አካካቢ) 500 አባወራ የሚገኙበት መንደር ከእንቅስቃሴ ታግዶ ተዘግቶል፡፡ ወደ መንደሩ በሚያስገባው ቅያስ ላይ ፖሊሶች እና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ቆመው ከነዋሪው ሌላ ሰው እንዳያልፍ ሲከለክሉ መመልከቱን ሬድዮ ጣቢያው ግልጿል፡፡

ለነዋሪው የአስቤዛ ፤ የፅህና መጠበቂያ ሳሙና ፤ሳኒታይዘር እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ አቅርቦቱ ከዚህ በፊት ለወረርሽኙ ተብለው ከተለያዩ አካላት ከተሰበሰበው እየተሸፈነ ይገኛል። በተለይም የአሊባባ ድጋፍ በእጅጉ እንዳገዘ የወረዳው አመራሮች ገልፀዋል፡፡

የስራቸው ሁኔታ ግድ ከቤት የሚያስወጣ ለሆነባቸው ነዋሪውች ለሚሰሩበት ተቋም የትብብር ደብዳቤ እየተፃፈ ነው፡፡

በዚህ መንደር የሚኖሩት ነዋሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ እዛው ባሉበት ተለይተው በመቆየት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የታለመ ነው፡፡ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል ግንዛቤ ለማስጨበጥ በተቋቋመው አደረጃጀት ውስጥ ያሉ በጎ ፍቃደኞችም የችግሩ ሰለባ ናቸው ተብሏል።

በዚያው ክፍለከተማ አምስተኛ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ በእስረኞች እና ጉዳይ በሚያስፈፅሙ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ንክኪ በአንድ የቫይረሱ ታማሚ ምክንያት 66 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

አዲስ ከተማ ክፍለከተማ እና ልደታ ክፍለከተማ ጤና ሚኒስቴር ፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ለዚህ ሲባል የተቋቋመው ግብረሃይል ከዚህ የበለጠ እንዳይሰራጭ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ በርካታ ሰዎች በሚኖሩበት በልደታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሁሉም ህንፃዎች ላይ ምርመራ ተደርጎል፡፡ ምርመራውን ሲሸሹ የነበሩ ሰውችንም ነበሩ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ ጣቢያ

Report Page