#COVID19

#COVID19


የኮሮና ቫይረስ በሽታ (የኮቪድ-19) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ፦

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ -19) ስርጭት

• በዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት እስከ የካቲት 20 /2012 ይህ መረጃ  እሰከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሰማንያ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ አስር (83,310) ሲሆን ሁለት ሺህ ስምንተ መቶ ሃምሳ ስምንት (2,858) ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡

• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ያሏቸው መሆኑን አዲስ ሪፖረት ያደረጉትን አገራትን ክሮሺያ፤ ስዊዘርላንድ፤ አልጄሪያ፤ ብራዚል፤ ግሪክ፤ ሰሜን መቆዶንያ፤ ሮማኒያ፤ ኖርዌይ፤ ጅዮርጅያ፤ ኔዘርላንድ፤ ሉቴኒያ፤ ኦስትሪያ እና ናይጄሪያ ጨምሮ በሃምሳ (50) ሀገራት ውስጥ ሪፖርት ተደርጓል::

• ከቻይና ውጭ ያሉ አገራት በየቀኑ ሪፖርት የሚደረጉ የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡

በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ያለ የዝግጅት ሁኔታ

በአጠቃላይ ከጥር 15/2012 ጀምሮ

• በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች ሶስት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ አንደ መቶ (372,100) በሙቀት መለያ (ኢቦላና ኮቪድ-19 በማጣመር) አልፈዋል፡፡

• በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ ሰባት (220,357) በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አምስት ሺህ አራት መቶ ስባ ስድስት (5,476) በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡

• ሰማንያ ሁለት (82) ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Public Health Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡

• ከነዚህም ጥቆማዎች ሀያ (20) የበሽታውን ተመሳሳይ ምልክቶችን በማሳየታቸው እና የቻይና ጉዞ ታሪክ ስለ ነበራቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ግለሰቦች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ሠዓት በለይቶ ማቆያ ውስጥ ተለይቶ ያለ በበሽታው የተጠረጠረ ሰው የለም፡፡

• በ8335 የነጻ የስልክ መስመር በአጠቃላይ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሁለት (3,922) ጥሪዎች የደረሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንድ ሺህ ሶስት መቶ አርባ (1,340) ከኮቬድ-19 ጋር የተገናኙ መረጃዎች ናቸው፡፡

ከባለፈው ጋዜጣዊ መግለጫ ማለትም ከየካቲት 17/2012 ጀምሮ ይህ መረጃ እስከ ተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ያሉ አዲስ መረጃዎች

• በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች አርባ ሰባት ሺህ አምስት መቶ አርባ አምስት (47,545) ሙቀት መለያ (ኢቦላና ኮቪድ-19 በማጣመር) አልፈዋል፡፡

• በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች ሃያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ (28,650) በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ስድስት መቶ ስድሳ (660) በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡

• በክትትል ላይ የነበሩ ነገር ግን 14 ቀናት የሞላቸው አምስት መቶ ሃያ ስምንተ (528) ሰዎች ክትትላቸው የጨረሱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ስምንት መቶ ሰባ አምስት (875) የሚሆኑት ደግሞ ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

• ስምንት (8) አዳዲስ ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Public Health Emergency Operation Center) የደረሱ ሲሆን በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ስራ ተደርጎ ሶስቱ የበሽታው ተመሳሳይ ምልክት በማሳየታቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን ለነዚህም የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ሁሉም ተጠርጣሪዎች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ስለተረጋገጠ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡

 በ8335 የነጻ የስልክ መስመር በአጠቃላይ አምስት መቶ ሰባት (507) ጥሪዎች የደረሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንድ መቶ ዘጠና ስድስት (196) ከኮቬድ-19 ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

በመካሄድ ላይ ያሉ ዋና ዋና ተግባራት

• የጤና አጋር እና ለጋሽ ድርጅቶች የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የሚገኘው የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል ጎብኝተው ከኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና ከቅርብ ዝግጁነት አስተባባሪ ጋር አጭር ውይይት አድርገዋል፡፡

• የቻይና ኢምባሲ የጤና ክፍል ሠራተኞች በኮቪድ -19 ላይ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ጋር መስራት የሚችሉበት ተግባራት ላይ ከኢኒቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ በኢኒስቲትዩቱ የሚገኘውን የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል ጎብኝተዋል፡፡

• ከዓለም የጤና ድርጅት፤ አፍሪካ ሲዲሲ (CDC) እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በኢትዪጵያ አየር መንገድ የበረራ ሰራተኞችን ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

• የበሽታውን ቅድመ ዝግጁነት ለማጠናከር ከተለያዩ ኢንደስትሪያል ፓርኮች ለተወጣጡ ዋና ዳይሬክተሮችን እና ባለሞያዎችን ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ 

• ከምላሽ ህከቻይና በተጨማሪ ከኮሪያ ፤ጃፓን ፤ከኢራን ኢስላማዊ ሪፐብሊክ እና ጣሊያን የሚመጡ ተጓዦችን የልየታ እና የህክምና ቅጽ በማስሞላት ክትትል ማድረግ ተጀምሯል

• በአፍሪካ የዓለም ጤና ድርጅት አማካሪ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የሚገኘውን የኢንፍሉዌንዛ ላብራቶሪ ግምገማ አደርገው ለኮቪደ -19 ምርመራ በቂ ደረጃ ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

• በአፋር ክልል ጋላፊ ኬላ ላይ የልየታ ስራ ተጀምሯል፡፡

• የተመረጡትን ለይቶ ማቆያ እና ህክምና መስጫ ሆስፒታሎች በመድሃኒት እና መከላከያ ግብአት በቂ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

• ከስልጠና ባለፈ የባለሞያዎችን ዝግጅት ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ በየግዜው የዝግጁነት ልምምድ እየተደረገ ይገኛል

ለኮሮና ቫይረስ በሽታ(ኮቪድ -19) የክልሎች ዝግጅት

የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ወደ ሃገራችን እንዳይገባ በሚደረገው ዝግጅት የክልል መንግስታት ዝግጁነት እና ፈጣን ምላሽ ወሳኝነት አለው፡፡ የክልሎችን ተሳትፎና ዝግጁነት ለማጠናከርና በየደረጃው እስከ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ለማውረድ ይረዳ ዘንድ የአቅም ግንባታ ስራዎች በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ተጠርጣሪ ህመምተኞችን ለይቶ በማቆያ እና ህክምና መስጫ ተቛማት የሚያስፈልጉ የህክምና እቃዎችን ማሟላት፤ 

በኢንተርናሽናል ኤርፖርቶች ላይ የሚካሄደውን የመከላከል ስራ በማስፋፋት በቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ባሉ የአየር መንገዶች የልየታ ስራ ለማስጀመር፤ በየክልሉ ያሉትን ተጓዦች እና ቫይረሱን ሪፖርት ካደረጉ አገራት የመጡትን ኢትዮጵያውያን የቅርብ ክትትል ማድረግ ይረዳ ዘንድ የክትትል ቡድን እና ጭምጭምታ የሚያጣራ ቡድን በየክልሉ ማዋቀር እንዲሁም በቫይረሱ ህክምና እና ቁጥጥር የሚሳተፉ ባለሞያዎችን ለማብቃት ስልጠና መስጠት ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም፤

• ከሁሉም ክልሎች ለተወጣጡ ባለሞያዎች ስልጠና ተሰጥቷል

• ከሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በሐዋሳ ከተማ ለይቶ ማቆያ ተመርጦ የተዘጋጀ ሲሆን በጂንካ እና አርባ- ምንጭ ለማዘጋጀት ስራ ተጀምሯል፡፡

• በጋምቤላ በጎግ፤ ዲማ፤ ላሬ፤ ዋንታዎ እና ጂካዎ በድንበር ኬላዎች ከሚደረግ የልየታ ስራ በተጨማሪ ከሆስፒታሎች ጋር በመተባበር የለይቶ ማቆያ እና የህክምና መስጫ ተዘጋጅቷል፡፡

• በአማራ ክልል በመተማ ድንበር እና ባህርዳር ዓለም አቀፍ አየር መንገድ የልየታ ስራ የተጀመረ ሲሆን በተመሳሳይ በላሊበላ፤ ጎንደር እና ኮምቦልቻ የልየታ ስራ ለመጀመር እና በእነዚህ ቦታዎች የለይቶ ማቆያ እና ህክምና መስጫ ለማቋቋም እየተሰራ ይገኛል፡፡

• በድሬደዋ ከተማ ካለው በዳወሌ ድንበር፤ በባቡር እና በዓለም አቀፍ አየር መንገድ የተጠናከረ የልየታ ስራ በተጨማሪ ከመከላከያ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የለይቶ ማቆያ ተቋቁሟል፡፡

• በኦሮሚያ ክልል ለከተሞች፤ ለዞን እና ለሆስፖታሎች ስለ ኮቪድ -19 ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በቢሾፍቱ እና በጅማ ለይቶ ማቆያ ተቋቁሟል፡፡ እንዲሁም በሐረማያ፤ በአዳማ፤ ሻሸመኔ፤ ያቤሎ እን ነቀምቴ ተመሳሳይ የለይቶ ማቆያ ለማቋቋም ስራ ተጀምሯል፡፡

• በተለያዩ ኢንደስትሪያል ፓርኮች እና ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ማለትም በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ አገራት ጉዞ የነበራቸውን ባለሞያዎች ለ14 ቀናት በራሳቸው መለያ ቦታ ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዳይቀላቀሉ የሚደረግ ለይቶ ማቆየት እና ክትትል የማድረግ እንዲሁም ለሰራተኞች ስልጠና መስጠት ይገኙበታል፡፡

ጥንቃቄ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች

የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ካለባቸው አገሮች የመጡ ከሆነ

• እራስዎን ከሌሎች ሰዎች እና ከቤተሰብ አባላት ለ14 ቀናት በማግለል ጤናዎን  ይከታተሉ!

• በየዕለቱ የጤናዎትን ሁኔታ ለመከታተል ለሚደውሉ ባለሙያዎች ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ይተባበሩ!

•ትኩሳት፣ ሳልና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመዎት ለአስቸኳይ የህክምና እርዳታ 8335 ይደውሉ፤

  በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎትን ክንድዎን በማጠፍ     

  ወይም በሶፍት ይሸፍኑ፤ እጅዎን በሳሙናና በውሃ ይታጠቡ!

• የኮሮና ቫይረስ በሽታ ነጭ ጥቁር የቆዳ ቀለም ሳይለይ ሁሉንም የሰው ዘር የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡

• አስካሁን የተረጋገጠ መድሐኒት ወይም ክትባት የሌለው በመሆኑ ሕብረተሰቡ ይህንን በመረዳት እና የጥንቃቄ መንገዶችን በማወቅ እንዲሁም በመተግበር በሽታውን እንዲከላከል ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡

• በተጨማሪም ህብረተሰቡ በሀገራችን እስከ አሁን በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው አለመኖሩን አውቆ ሳይዘናጋ የበለጠ ጥንቃቄ ኢንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡

[የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት]

Report Page