#COVID19

#COVID19


ሀገር ዓቀፍ፦

• በአጠቃላይ ከጥር 15/2012 ጀምሮ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች 191,707 በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 4,821 በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች 324,555 በሙቀት መለያው (ኢቦላና ኮቪድ-19 በማጣመር) አልፈዋል፡፡ 

• ከባለፈው ጋዜጣዊ መግለጫ በኋላ ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች 45,350 በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 920 በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ 

• ከሳምንቱ ጋዜጣዊ መግለጫ በኋላ በክትትል ላይ የነበሩ ነገር ግን 14 ቀናት የሞላቸው 390 ሰዎች ክትትላቸው የተቋረጠ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 829 የሚሆኑት ደግሞ ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ 

• ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ 12 አዳዲስ ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Public Health Emergency Operation Center) የደረሱ ሲሆን በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጎ የበሽታውን ምልክት ያላሳዩ መሆኑ ተረጋግጧል፡:

• በአጠቃላይ ከጥር 15/2012 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 72 ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Public Health Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡

• ከነዚህም ጥቆማዎች 18ቱ የበሽታውን ምልክቶችን በማሳየታቸው እና የቻይና ጉዞ ታሪክ ስለነበራቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም 18 ቱንም የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡

• በ8335 የነጻ የስልክ መስመር አጠቃላይ 3,533 ጥሪዎች የደረሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 1,131 ከኮቬድ-19 ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ 878ቱ ከባለፈው ጋዜጣዊ መግለጫ በኋላ የደረሱ ሲሆኑ 332ቱ ከኮቬድ-19 ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

• በኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የሚመራው የቴክኒክ ግብረ ሀይል ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ የተለያዩ አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡

• የኢንስቲትዩቱ እና የክልል የድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ሰጪ ማዕከል አስተባባሪዎች ስብሰባ አካሂደዋል፣ በሲዲሲ አፍሪካ ድጋፍ ባለሙያዎች ወደ ውጭ ሀገር ሂደው ስለ ድንበር ቅኝት እና ኬዝ ማኔጅመንት ሰልጥነዋል፡፡

• ለሁሉም ከልሎች አስፈላጊውን ግብዐቶች በማሟላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እየተሰጡ ይገኛል፡፡

• የተለያዩ ፕሮቶኮሎች ተዘጋጅተው ለሚመለከታቸው ተሰራጭተዋል፡፡

Report Page