Corona Virus ፪

Corona Virus ፪

Deacon Yohannes @JohnDPT27
Bitcoin

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ

አምላክ አሜን

January ላይ በChina Wuhan ከተማ ቫይረሱ ከተነገረ ጀምሮ cryptocurrencies አንዱ የሆነው Bitcoin በ10% እንዲያድግ አስችሎታል፥ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ግን ግልፅ መረጃ የለንም፤ እንደ Adidas ያሉ Companies 20% ምርታቸው(ድርጅታቸው) በቻይና ከመሆኑ እና ቫይረሱ በመላው ዓለም በመስፋፋቱ ምክንያት $2Billion ብር እንዲከስር አድርጎታል እንዲሁም ፥ በአሜሪካ የመንገድ እና ትራንስፖርት ሚንስቴር በዚህ በሽታ ምክንያት $24 billion እንደከሰረ ገልጿል። እንደ WHO(world health organization) ገለጻ ከሆነ አንድ መቶ ሃያ ስምንት ሃገራት ውስጥ ቫይረሱ ገብቷል። ቻይና እንኩዋን እንደ ጊንጥ፣ አይጥ፣ አህያ ፣ውሻ መብላትን በህገ መንግስቷ እስክታግደው ድረስ አስገድዷታል፥ሃያላን ሃገራት ድንበራቸውን፣አለም አቀፍ በረራቸውን፣ ፌዝቲቫላቸውን እንዲሁም እንደ ጣልያን ያሉት ሃገራት ደግሞ ጭራሽኑ ሰው ከሰው እንዳይገናኝ እስከ ማገድ ደርሰዋል። ቫይረሱ እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት ክትባት ሆነ መድኃኒት የለውም። የአለማችን እውቅ እና ባለስልጣን የሆኑ ሰዎችን ጭምር አሽመድምዶ ይዝዋል። ለምሳሌ እስከ አሁን 9 የሚሆኑ የተለያዩ ክለቦች የኳስ ተጫዋቾች ተይዘዋል ይህ ብቻ ሳይሆን የአርሰናል አሰልጣኝ ጭምር በቫይረሱ ተይዝዋል። የኢራን የጤና ሚኒስቴር ፣ የብርታንያ የጤና ሚንስቴር ፣የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስቴር ባለቤት፣የስእስፔን ፕሬዝዳንት ባለቤት፣የሞሮኮ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ፣በአሜሪካ የብራዚል አምባሳደር ፣ የፈረንሳይ የባህል ሚኒስቴር በቨይረሱ ተይዘዋል። ዩንቨርስቲ ፣ ትምህርት ቤቶች ፣ሆቴሎች ፣ ምግብ ቤቶች በሙሉ ተዘግተዋል። ምን ይሻላል ? ? እንደ ኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር ፬ /፯/፪፻፲፪ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር Corona virus ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱን ስትናገር ፈራችሁን ? ደነገጣችሁን? ወይስ ድሮ እኮ ነው የገባው ውሸታሞች አላችሁ? ወይስ አለቀለልን በቃ አላችሁ ? የአስራት ሃገር ኢትዮጵያማ ቫይረሱ አይነካትም ያላችሁ ገብቷል ስትባሉ ምን አላችሁ ? የሚጠብቀን አያንቀላፋም ያላችሁ ቫይረሱ ገብቷል ስትባሉ ምን ትሉ ይሆን?

ዓለማችን እየወሰደች ያለችው መፍትሄ፦

፩~ አለመጨባበጥ

፪~ አፍን በማስክ ማፈን

፫~ እጅን መታጠብ

፬~ ከቤት አለመውጣት

ታድያ ግን ይህን እያደረግን የት ደረስን ? ቫይረሱ እንደሆነ በቁሶች ላይ ሳይቀር እስከ 6 ቀናት ይቆያል፣እንደ አሜሪካውያን ሳይንቲስቶች ደግሞ አየር ላይ ጭምር መቆየት እንደሚችል አስታውቀዋል፣በንክኪም፣በአየርም፣በትፏሽም ይተላለፋል። ታድያ ምን እናድርግ ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ መፍትሄ አለኝ ተከታተሉኝ።

Saint Abram

ጳጳስ አብረሃም ይባላሉ። የሚታወቀው ስማቸው ደግሞ "የደሆች ጓደኛ" በመባል ነው። ጳጳሱ የኖሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ 1829~1914 ዓ.ም ነው ። የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ጳጳስም ነበሩ፤ እኚህ ጳጳስ ታድያ ከዲቁና እስከ ምንኩስና ድረስ በደግ ምግባራቸው ዘልቀው የገፉ ናቸው። የቅድስት ድንግል ማርያም ገድም(El-muharraq)የገዳሙ አስተዳዳሪ ሆነው ሲሾሙ በ19 ዓመታቸው ነው። እኚህ ቅዱስ የሚያስተዳድሩትን ገዳም የድሆች መናኽርያ መጠግያ መሸሸግያ አደረጉዋት፥ሌሎች ግን በክፋት እንዲነሱ ከገዳሙ አደረጓቸው ። እኚህ አባት ገዳም ሲሾሙ አባ ጳውሎስ ዘገዳመ ማርያም ተብለው ተሰየሙ። በ1881 ዓ.ም በፓትርያርኩ እጅ ጵጵስናን ተቀብለዋል። ስማቸውም ተቀይሮ አቡነ አብረሃም ተብለው ተጠርተዋል። እኚህ አባት ከሰሯቸው ተዓምራት ውስጥ አንዱን ይህ ነው" በ1891 ዓ.ም ግብፅ እንደዛሬው ኮሮና ወረርሺኝ በሚመስል መልኩ ኮሌራ በሚሉት በሽታ ብዙ ሰዎችን ማጣት የጀመረችበት ግዜ ነበር፥በሽታው የብዙ ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ መንግስትም ከአቅሙ በላይም ሆነ በዚህ ክፉኛ የተጨነቁ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ምዕመናን በሌሊት ወደ ቅዱስ አባታችን አቡነ አብረሃም ዘንድ ሄዱ፥ታድያ ከተማዋን የረበሻትን Horror የሆነ በሽታ ነገሯቸው፥ቅዱሱ አቡነ አብረሃምም በጥሞና ካዳመጡ በኁዋላ እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው " ልጆቼ ለምንድን ነው ለመሞት ምትፈሩት? ዛሬ ባንሞትም ነገ እንሞታለን" ብለው ቀለል አድርገው መለሱላቸው። ከዛም እሳቸው አባ ሚካኤልን እንዲጠሩላቸው አዘዙ(የስጋ ወንድማቸው)። አባ ሚካኤልም በደረሱ ግዜ ቀጭን ትዕዛዝ በቆራጥ ልብ አስተላለፉ! ትዕዛዙም 200 ነጭ ወረቀት እንዲያመጡላቸው አዘዟቸው፥እሳቸውም እንደታዘዙት ተሸክመው ይዘው መጡ፥አቡነ አብረሃምም በእያንዳንዱ 200 ነጭ ወረቀት ላይ "እኛ የተሰቀለው የናዝሬቱ ኢየሱስ ባርያዎች ነን" የሚል ፅሁፍ እንዲጻፍበት አዘዙ፥ ከዛም በመቀጠል መስቀል እንዲታተምበት በማስደረግ በወረቀቶቹ ላይ ያለ ማቋረጥ ጸሎትን ከዕንባ ጋር በንፁህ ልቡና አቀረቡ። እያንዳንዱን ወረቀት ምዕመናኑ በር ላይ እንዲለጠፍ ትዕዛዝ ሰጡ።(የሙሴን አርዓያ ያደረጉ ይመስላል"፤ እግዚአብሔር ግብፃውያንን ይመታ ዘንድ ያልፋልና፤ ደሙንም በጉበኑና በሁለቱ መቃኖች ላይ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር በደጁ ላይ ያልፋል፥ አጥፊውም ይመታችሁ ዘንድ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይተውም።" (ኦሪት ዘጸአት ፲፪ ፥ ፳፫ ) እያንዳንዱ ሰው ይህን ወረቀት በሩ ላይ የለጠፈ ኦርቶዶክስ የኮሌራው በሽታ እያለፈው ይሄድ ነበር፤በዚህም የ 200 ሰዎችን ነፍስ ከሞት ታድገውታል ። የአባታችን አቡነ አብረሃም ጸሎታቸው ልመናቸው አይለየን። ይህ ተዓምር በግብፅ synxarium (መጽሐፈ ስንክሳር) ላይ ተፅፎ ይገኛል። በግብፅ ቀኖና መሰረት አንድን ሰው ቅዱስ ብሎ ለመጥራት 50 ዓመት ከሞተ በኁዋላ መጠበቅ ይገባልና፥አቡነ አብረሃምም በ1964 ዓ.ም ከሞቱ ከ50 ዓመት በኁዋላ በፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ዘመን ቅዱስ መሆናቸው ታውጆላቸዋል፥ስንክሳር ላይም ሰፍረዋል።በስማቸው ገዳም ተመስርቶላቸዋል። እኚህ ቅዱስ ትንቢት ተናግረው ተፈጽሞላቸውል ፣ የባለስልጣን ልጅ ፈውሰዋል ፣ ሙት አንስተዋል ፣አጋንንት ቅድስናቸውን መስክሮላቸዋል የብዙ ብዙ ተዓምራትን አድርገዋል ይህ የሆነው በሃገራችን አጼ ቴውድሮስ በነገሰ 4ቱ የግብፅ ጳጳሳት በተላኩ ግዜ ነው።

ከእኛ ምን ይጠበቃል ከቅዱስ

——ሲኖዶስስ ?——


ምልዐተ ሲኖዶስ

ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት የቅድስት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪ፣ጉልላትዋ፣አካልዋ፣መዋቅርዋ ነው ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ ነውና የሚመራው። ታድያ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ ቅዱስ አብረሃም ያሉ አባቶችን በዚህ ዘመን ማስነሳት አለበት፥ ህዝቡን ከመቅሰፍት፣ከበሽታ፣ከምንፍቅና ፣ ከተሃድሶው ፣ ከአህዛቡ እንዲሁም ከጠላት ሃይላት መጠበቅ ይኖርበታል !

ኦርቶዶክስ ምዕመን ሆይ ዘመኑ ብዙ ተኩላዎች የበዙበት ነውና ተጠንቀቁ ! ማንም እንዲህ ትሆናላችሁ ባላችሁ ቁጥር አትረበሹ ምን ግዜም ምዕመናን ፀሐይ ክርስቶስን እንዲሞቁ፣ሰማያዊ ክርስቶስን እንዲለብሱ፣ረቢ ክርስቶስን እንዲማሩት፣ኅብስት ክርስቶስን እንዲመገቡት፣ ጽዋ ክርስቶስን እንዲጠጡት፣ህይወት ክርስቶስን እንዲኖሩት፣ሰማይ ክርስቶስን እንዲያዩት፣ፍኖተ ጽድቅ ክርስቶስን እንዲሄዱበት ያስፈልጋል ! ክርስቲያን ምን ግዜም መልኩ ዘክርስቶስ፣ኑሮው ዘክርስቶስ፣ ትዳሩም ዘክርስቶስ፣ ሲሞትም ዘክርስቶስ መሆን መቻል አለበት ። ቅዱስ ሲኖዶስ እንዳያንቀላፋ ከፈለግን እንደ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ምዕመናን አባቶችን ሄዶ በመጠየቅ ማንቃት ይኖርብናል። አሁን ሆድ እና ጀርባ የሆንን ይመስላል፥ምዕመን ስለ ቤተክርስቲያን የሚያውቀው ነገር የለም አባቶችም ምዕመናኑን አያውቁትም ! እንድንተዋወቅ እርስ በእርሳችን እንፈላለግ ! ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ የቅዱስ አብረሃምን ተሞክሮ መውሰድ አለባቸው "ዛሬ ባትሞቱ ነገ ትሞታላችሁ" ——⊙ በማለት ክርስቲያኑን ሞትን እንዳይፈራ ማጀገን አለባቸው ! እናንተም ንስሃ ከገባችሁ፣ክቡር ስጋውን ክቡር ደሙን ከተቀበላችሁ ሞትን አትፈሩትም! Corona virus አያስጨንቃችሁም !

ጌታችንም በወንጌል"ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው" (የማቴዎስ ወንጌል ፲፯: ፳፩) ስለዚህ እናንተም "ይህ ዓይነት Corona Virus ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም እላችኋለሁ" እንጂ እጃችሁን ለ20 ደቂቃ ስለታጠብን ፣ አፋችንን ስለሸፈንን አይደለም።

የጸሐፊው ማሳሰብያ

📌ጠቅላይ ሚንስቴሩ 100 ሚልዮን ብር ለCorona Virus ማጥፊያ ሰጠዋል፣አሜሪካ አንበጣ መንጋ ለማጥፋት 10 ሚልዮን ዶላር ለግሳለች ነገር ግን የቱ መንገድ ይቀላል?በጸሎት እንደ ቅዱስ አብረሃም ድል መንሳት ወይስ ሚልዮን ብር መፍጀት ?መልሱን ለእናንተው ትቼዋለው !📌

{——"፤ ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፥ ማስተዋልም ይጋርድሃል፥" (መጽሐፈ ምሳሌ ፪: ፲፩)——}

ከመንፈሳዊነት ባሻገር ደግሞ በበኩላችን ጠቢቡ እንዳለው መጠንቀቁ እና ማስተዋሉም አይከፋም! መሠረቱ ግን መንፈሳዊነት ነው ጥንቃቄውም ከዚህ ጋር አብሮ ነው የሚሄደው። ስለዚህ Who ያወጣውንም የመከላከያ ስርዓት መከተል ያስፈልጋል። እንዲሁም የጣልያኑ መሪ እንደተናገሩት " ውድ የጣሊያን ህዝቦች ሆይ ለዚህ ግዜ ስንል ለትንሽ ወራት ባህላችንን እንተው " ባሉት መሠረት እናንተም ኢትዮጵያውያን ባህላችንን ለትንሽ ግዜ እናቆየው ህዝብ ብዛት ከሚገኝበት አለመሄድ፣ እጅን በአግባቡ በንፅህና መጠበቅ፣ ልብሳችንን በየቀኑ ማጠብ፣ አፍን መሸፈን፣ በእጃችን ሰላምታን አለመሰጣጣት እና የመሳሰሉትን ጥንቃቄዎች መውሰድ ተገቢ ነው ።

መዝ ፮ ፥ ፩ ድገሙ——

"እግዚኦ በመአትከ ኢትቅስፈኒ ወበመቅሰፍትከ

—— ኢትገስፀኒ"




+ዲያቆን ዮሃንስ+

+አዲስ አበባ ፮ / ፯/ ፪፻፲፪+

+እልመስጦአግያ+

@JohnDPT27

@Learn_With_John

Report Page