Computer

Computer

@tech_info2

‍ ✳️‍ መሰራታዊ 💻 የኮምፕዩተር እውቀት፤ ኮምፒዩተር ምንድነው?

🔰 #ኮምፒውተር ማለት በሰውም ይሁን በፕሮግራም በታዘዘው የተለያዩ #ትእዛዞች መሰረት ስራ የሚያከናውን #ማሽን ነው፡፡ ይህ ስራ ለምሳሌ #ሰነድ ለመጻፍ፣ #ሂሳብ ለማሰል፣ #ኢንተርኔት ለመጠቀም፣ #ለመጫወት ፣ #ፎቶና ቪዲዮ ለማዘጋጀት ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን የስራ ክንውን ለመፈጸም #ኮምፕዩተር #በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ከታች የቀረቡት ሶስቱ መሰረታዊ ክፍሎች ኮምፕዩተሩ እንደ #ኮምፕዩተር እንዲሆንና #ትእዛዞቹም እንዲፈጸሙ ያስችሉታል፡፡ በአይነትም ሆነ በትልቅነት የተለያዩ ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የጭን፣ የቤት፣ የመስሪያ ቤት ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ከአካል #መጠናቸው፣ ከፍጥነታቸውና ከአቅማቸው ልዩነት በስተቀር መሰረታዊ #አሰራራቸው ይመሳሰላል፡፡


💡አንደኛው 

#የውስጥ አካላዊ ክፍሎቹ ለምሳሌ Harddrive HD ፣ #RAM ፣ #Motherboard ፣ #Sound card ፣ #Video card፣ #CPU ይገኙበታል፡፡ እና #የውጭ አካላዊ ክፍሎቹ ደግሞ #Display ፣ #Keyboard ፣ #CD/DVD-rom ፣ #Printer ፣ #Mouse ፣ ይገኙበታል፡፡ የሁሉም የውስጥና የውጭ አካል የጋራ ስም ደግሞ #ሃርድዌር ይባላል፡፡ ይህ ሃርድዌር #በአካል የሚታይና የሚነካ ነው፡፡


💡ሁለተኛው

#አካላዊ ያልሆኑ ፕሮግራም ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህም ለምሳሌ #ሰነድ መጻፊያዎች፣ #ሂሳብ ማስሊያወች፣ #ኢንተርኔት መጠቀሚያዎ ፣ #ስእል መሳሊያወች፣ #ፎቶና ቪዲዮ ማቀናበሪያወች ወዘተ የሚያገለግሉ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደተጠቃሚው ፍላጎትና ስራ #በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የሁሉም ፕሮግራሞች አጭር የጋራ ስም #software ሊባል ይችላል፡፡ ሶፍትዌር ልክ እንደ #ሃርድዌር የሚነካና #የሚጨበጥ አይደለም፡፡ 



💡ሶስተኛው

# Operating System ዋና ዋና ሚና ካላቸው አንዱ ክፍል ነው፡፡ ባጭሩ ዋናው የ #Operating System ስራ ግን #;የኮምፕዩተር የውስጥና #የውጭ አካል እና #ሶፍትዌሮች በአንድ ላይ ተጣጥመው ወይም #እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡ ለምሳሌ #Windows ፣ #Mac ፣ #Linux የመሳሰሉት #Operating System #አይነቶች ናቸው፡፡


#ኮምፕዩተሩ እንዲሰራ ሶስቱም ክፍሉች ማለትም #አካላዊ ክፍሎቹ፣ #ፕሮግራሞቹና Operating System በአንድ ላይ ተቀናጅተውና #ተስማምተው መስራት አለባቸው፡፡ 


‍ ✳️ Power Supply 


#የኤሌክትሪክ ሃይልን መጥኖ #ለተለያዩ የአካል ክፍሎች ማደል ነው፡፡ ሁሉም #የኮምፕዩተር አካል ክፍሎች #አንድ አይነት የኤሌክትሪክ ሃይል #(ቮልት) አይጠቀሙም፡፡ ስለዚህ የሃይል #አዳዩ ቮልቱን መጥኖ ለሁሉም ክፍሎች ይልካል፡፡ #ለምሳሌ 12 ቮልት፣ 9 ቮልት፣ 6 ቮልት፣ 48ቮልት ሊሆን ይችላል፡፡ #ፓወር ሳፕላይ እራሱን የቻለ #ማራገቢያ አለው #Power Supply Fan ይባላል፡፡

‍ ‍ ✳️ Hard drive HD HHD 


#ዳታዎችን በቋሚነት #ለመያዝ ነው፡፡ #የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) #የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት #ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት #የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ የሆነ #ሰነድ ጽፈው ለመያዝ ከፈለጉ የሚይዘው #HHD ላይ ነው፡፡ እንደተለመደው HHD ዋና ቦርድ ላይ የሰካል፡፡ HHD ዳታ ሲያነብና ሲጽፍ #ማግኔታዊ ነው፡፡

‍ ✳️ Random Access Memory RAM


#ራም የሚጠቅመው #የተቀሰቀሱ/የተከፈቱ #ፕሮግራሞች #በፍጥነት እንዲነዱ የሚጠቅም ነው፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው #ኮምፕዩተሩ እነዚህን የተቀሰቀሱ #ፕሮግራሞች ለጊዜው (ተቀስቅሰው እስካሉ ድረስ) ለምሳሌ #HHD ወይም ከሲዲ ከማንበብ ይልቅ ከራም ላይ ያነባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ራም #ጊዚያዊ ፕሮግራም ተሸካሚ ግን በፍጥነት አቅራቢ እንደማለት ነው፡፡ #ለምሳሌ አንድ ተጠቃሚ ኢንተርነት የሚቀዝፍ ከሆነ ቀዛፊውን ከፍቷል፡፡ ሰነድ የሚጽፍ ከሆነ ወርድን ከፍቷል #ፎቶ ወይም ቪዲዮ የሚሰራ ከሆነ የፎቶና ቪዲዮ #ፕሮግራሞች ከፍቷል፡፡ እና እነዚህ ፕሮግራሞች #እስከተከፈቱ ድረስ #ራም ለጊዜው ተሸክሞ ይይዛቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ራም ከፍ ባለ ቁጥር #የኮምፕዩተሩም #ፍጥነት የሚጨምረው፡፡ ያው አማካይ አዛዢም እራሱን የቻለ ሚና ቢጫወትም፡፡ #ራም ልክ እንደሌሎቹ ክፍሎች ዋና ቦርድ ቦታ ስላለው እዛ ይሰካል፡፡


‍ ✳️ CD/DVD-Rom 


#እንደሚታወቀው #ሲዲ/ዲቪዲ ላይ ሙዚቃ/ቪዲዮ/ፎቶ/ሶፍትዌር (ዳታ) የመሳሰሉትን #ለማንበብ ነው፡፡ #የሲዲ/ዲቪዲ ቤቱ ከዋናው ቦርድ ጋር #እንዲገናኝ እንዲሁም #ትእዛዝ እንዲቀበልና እንዲልክ በብዙ #Cable ከዋና ቦሩዱ ጋር ይያያዛል፡፡


‍ ✳️ Central Processing Unit CPU 


#የኮምፒውተሩ #አዕምሮ ነው፡፡ CPU #ከሃርድዌርና #ከሶፍትዌር የሚመጡትን ትእዛዞች ለማስተናገድ ሃላፊነት አለበት፡፡ በአንድ ሰከንድ ውስጥ #በሚልዮን የሚቆጠሩ ትእዛዞችን ማስተናገድ ይችላል፡፡ #CPU የተለያዩ #ትእዛዞችን በፍጥነት ስለሚያተናግድና #ስራ ስለሚበዛበት #በጣም ይሞቃል፡፡ ስለዚህ እራሱን የቻለ ማራገቢያ #(CPU) ካናቱ ላይ አለው፡፡

ትእዛዙንም #ለማስተላለፍ ዋናው ቦርድ ላይ በብዙ እግሮቹ ተሰክቶ ይቀመጣል፡፡ #CPU ከሌሎች አካሎች በበለጠ እጅግ በጣም ውስብስብ በሆነ #ቴክኖሎጂ የተሰራ ነው፡፡

Join Chanal @tech_info2

Admin @Khiladi_lingard14bot


Report Page