Check

Check

ATC

በትምህርት ቤቶች ኮሮናን ለመከላከል መምህራን ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡

…………………………………………

የትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ 19 ተፅዕኖን በመቋቋም ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት የሚያስቸሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ እንዳለ የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ/ዶ/ር ኢንጅ/ ገልፀዋል፡፡


የኮሮና ቫይረስ በመቋቋም ትምህርት ለመጀመር በሚደረግ ጥረት ውስጥ የመምህራን ድርሻ የጎላ መሆኑ ተገልጿል፡፡


ሚኒስትሩ እንደ ጤና ባለሙያዎች ሁሉ ኮሮናን በመቋቋም ትምህርት ለመጀመር በሚደረግ ጥረት መምህራንም ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል።


መምህራን በመማር ማስተማሩ ሂደት የሚኖሩ ጫናዎችን ተቋቁመው መደረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲያከናውኑ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።


ትምህርት ሚኒስቴር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር የሚያደርገው ውይይት እንደ ቀጠለ መሆኑን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡


#MoE

@amharictutorialclass

@amharictutorialclassbot

Report Page