Cf

Cf

Zaman 888

ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ በሦስትነት ለሚቀደስ

በአንድነቱ ለሚመለክ፣ መቅደሱ እንሆን ዘንድ አስቀድሞ ላዘጋጀን፣ ከሰማይ

መላእክት ከምድር ፍጥረታት ሁሉ ይልቅ አልቆ በእርሱ አርዓያና አምሳል

ለፈጠረን ለእርሱ ለሥላሴ ክብር ምስጋና ይሁን፡፡

አይሁድ ጌታችንን በጥፊ ጸፍተው፣ ርኩስ ምራቃቸውን ወርቀውበት፣ ቀይ ግምዣ

ልብስ አልብሰው ዘብተውበት፣ አጥንቱ እስኪታይ ድረስ ገርፈው፣ የእሾህ አክሊል

ደፍተው፣ መስቀሉን አሸክመው፣ በጭካኔ በመስቀል ላይ ቸንክረው ገደሉት፡፡

ጌታችን ግን በእርሱ ላይ በፈጸሙት ግፍ በአይሁድ ላይ ተቆጥቶ ሊያጠፋቸው

አልወደደም፡፡ ነገር ግን “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለት

የእነርሱን ጥፋት እንደማይሻ ገለጠላቸው፡፡

ለምን እንዲህ አደረገ ብለን ብንጠይቅ ቅዱስ ጳውሎስን የመሰሉ ቅዱሳን

ከእነርሱ ወገን ስለሚወጡ ስለ እነርሱ ሲል በቀሉን ማዘግየቱን እንረዳለን እንጂ

መቼም በሥጋ ከእነርሱ ወገን ስለተወለደ ለወገኑ ሳስቶ አይደለም፡፡ እንዲህም

ስለሆነ በዚያ “ደሙ በእኛና በልጅ ልጆቻችን ላይ ይሁን” ባለው ክፉ ትውልድ

ላይ እንደርሱ ከፉና አረመኔ በሆነ ወገን እና ሰውን መግደል ትንኝን

እንደመጨፍለቅ ቀላል ለሚመሰለው ለጥጦስ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ የክርስቶስም

የበቀል ክንድ በእነርሱ ላይ አረፈ፡፡ እንዲህም ማድረጉ በእርሱ ላይ በክፋት

ስለተነሡና እርሱን ሰቅለው ስለገደሉ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ይህ ይቀበል ዘንድ

ሰው ሆኖአልና ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው፡፡ ነገር ግን በክፋታቸው ስለ ጸኑ፣

ከእግዚአብሔር ይልቅ ለዲያብሎስ ፈቃድ ስላደሉ፣ እግዚአብሔር ያን ትውልድ

በጥጦስ አጠፋው፡፡

እንዲሁ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወይም በተዋሕዶ ልጆች ላይ ወይም በክርስቶስ

የአካሉ ሕዋስ በሆነው ላይ ወይም በክርስቶስ አንድ ሰው በተባልነው በእኛ ላይ

በጥፋት የሚነሣ አካል ሁሉ በክርስቶስ ላይ በክፋት ተነሣሥቶአልና በንስሐ ከዚህ

ክፋቱ ካልተመለስ ክርስቶስ ተበቅሎ እንደሚያጠፋው ይወቅ፡፡

እንደ ምሳሌ፡- ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ ክርስቲያኖችን አሳዳጅ ነበር፡፡ እናም

ክርስቲያኖችን እያሳደደ ሳለ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደማስቆ

መንገድ ላይ ተገልጦለት “ሳውል ሳውል ሆይ ስለምን ታሳድደኛለን ብሎ” ማንን

እያሳደደ እንዳለ እንዲረዳ አደረገው፡፡ ምክንያቱም ክርስቲያኖቶችን ማሳደድ

ማለት ክርስቶስን ማሳደድ በእነርሱ ላይ በክፋት መነሣት ማለት ነውና፡፡

እንዲህም ስለሆነ እናንተ እኛ ላይ ለጥፋት የዘመታችሁ መንግሥትና የክርስቶስ

ጠላቶች ስለ እኛ የሚዋጋ ክርስቶስ አለና እርሱ እንደ አይሁድ እናንተንም ተበቅሎ

የሚያጠፋበት ጊዜ አለውና ልብ ግዙ፡፡ ከዚህ ክፋት ድርጊታችሁ ተመለሱ፡፡

እንዲሁ በዚህ ክፉ ሥራቸው ተባባሪ የሆናችሁ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኛችሁ

የመንግሥት ሹመኞችና በእነርሱ ጉያ ወስጥ ተሸጉጣችሁ ያላችሁ የተዋሕዶ

ልጆች ከክርስቶስ በቀል ራሳችሁን ታድኑ ዘንድ ስለ ቤተ ክርስቲያን አጥፊዎችን

በግልጽ ተቃወሟቸው፡፡ ከእነርሱ ክፋት ሥራ ጋር ብትተበበሩ ወይም ቸል ብላችሁ

ቤተ ክርስቲያን ስትፈርስ ካህናትና ዲያቆናት ሲታረዱ እየሰማችሁ እያያችሁ

ፖለቲካው በልጦባችሁ ዝምታን ብትመርጡ ግን አብራችሁ እንድትጠፉ እወቁ፡፡

ክርስቶስ ምን እንዳለ ላስታውሳችሁ “የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው

ነበረ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፥ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች

አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። የሚያፈራበትም ጊዜ ሲቀርብ፥ ፍሬውን ሊቀበሉ

ባሮቹን ወደ ገበሬዎች ላከ። ገበሬዎቹም ባሮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት

አንዱንም ገደሉት ሌላውንም ወገሩት። ደግሞ ከፊተኞች የሚበዙ ሌሎች

ባሮችን ላከ፥ እንዲሁም አደረጉባቸው። በኋላ ግን፦ ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ

ልጁን ላከባቸው። ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው፦ ወራሹ ይህ

ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ። ይዘውም ከወይኑ አትክልት

አወጡና ገደሉት። እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ በእነዚህ

ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል? እነርሱም፦ ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፥

የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች

ይሰጠዋል አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ

የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው የሚለውን

ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን? ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር

መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።

በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ

ይፈጨዋል።” አለ፡፡ ይህ ቃል ምንም እንኳን ለጊዜው ለጸሐፍት ፈሪሳውያን

ይነገር እንጂ የክርስቶስ አካል በሆነች ቤተ ክርስቲያን ላይ በጠላትነትም

በተነሣችሁ በእናንተም ላይ እንደሚሠራ እወቁ፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ክርስቶስንና

አገልጋይ ካህናትን ነበርና የገደሉት፡፡ እነዚያ ወገኖች የራሳቸው ሥጋዊ ጥቅም

እንዳይነካባቸው ሲሉ በክርስቶስ ላይ ተነሣስተው ገደሉት፡፡ እናንተም እንዲሁ

በዘረኝነት ታውራችሁ ሰይጣን አገብሮአችሁ ነው፣ የክርስቶስ አካል በሆነች ቤተ

ከርስቲያን ወይም በክርስቶስ ባመኑት ምእመናን ላይ ተነሠታችሁ ገድላችሁ

ስታበቁ አጋድማችሁ አረዳችኋቸው፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ተበቅሎ እንዲያጠፋችሁ

እወቁ፡፡

ጥንትም በምናብ የፈጠራችሁትን አምላክ ብላችሁ ክርስቶስን ጠላት አድርጋችሁ

የተነሣችሁ ነበራችሁ፡፡ ይህን ምናባዊ አምልኳችሁን በእኛ ላይ በማባበል

ለመጫን ሞከራችሁ በሙግት ሞከራችሁ አልሆነላችሁም፣ ይህ ጥረታችሁ

የእናንተን ሰይጣን አምላኪነት ሰለገልጥባችሁ ባይሆንላችሁ በቤተ ክርስቲያንና

በልጆቿ ላይ የመጨረሻ ዝናራችሁን ታጥቃችሁ የመንግሥትን ቁልፍ የሥልጣን

ቦታዎችን በመያዝ ሥጋችንን ልትገድሉ እና ቤተ ክርስቲያንን ልታቃጥሉ

ተነሣችሁ፡፡ ክርስቶስ ግን ለእኛ እንዲህ እንዳለን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ፡-

“ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፣ ይልቅስ

ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ፡፡”(ማቴ.10፡28) ስለዚህ

ሥጋችንን በመግደል ቤተ ክርስቲያንን በማቃጠል እኛን ለማስፈራራትና

ለማጥፋት ብትሞክሩ አይሳካላችሁምና አትድከሙ፡፡ እኛ እንድንፈራው የታዘዝነው

“ሥጋንም ነፍስንም ወደ ገሃነም የሚጥለውን እግዚአብሔር” ብቻ ነው፡፡ እርሱም

ከእናንተ ጥፍር ያድነናል፡፡ እንዲህም ሲባል ግን እርሱ ያድነናል ብለን በከንቱ

እንደ የዋኀን በጎች(መዝ.48(49)፡14) አንገታችንን ሰጥተን የምንታረድላችሁ

እንዳልሆነ ተገንዘቡ፡፡ ከአምላካችን ጋር ቆመን እንዋጋችኋለን እንጂ፡፡ ይህ ነው

የእኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች መርህ፡፡ በዚህ

መርህም ለእነርሱ አሽከር ከሆናችሁላቸው ከምዕራባውያን ጋር በአድዋ ላይ

ውጊያ ገጠምን በእርሱ እርዳታ ድል ነሥተን አሳፍረን መልሰናቸው፡፡

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በእርሷ ላይ ለተከፈተው የተቀናጀ ዘመቻ አማኞቿ ጾምና

ጸሎት ይዘው ከአምላክ ጋር እንዲሰለፉ የጾምና የጸሎት እንዲሁም የምሕላ

አዋጅ ልታውጅ ይገባታል፡፡ አሁንም ጊዜው አልረፈደምና የጾምና የጸሎት

እንዲሁም የምሕላ አዋጅ በማወጅ ምእመናን አንድ መንፈስና አንድ ልብ ሆነው

ቤተ ክርስቲያንን ከአምላክ ጋር በመሆን እንዲጠብቁ ትዘዝ፡፡ እውነት ነው፡-

“በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን

ሁሉ ይፈጨዋል” በክርስቶስና በመንጋው ላይ የሚነሣ ይቀጠቀጣል፤ ክርስቶስ

ለበቀል የተነሣበት ግን ይፈጫል፡፡

Report Page