Cc

Cc



Jdbdb

Dn Yohannes (jo):

❖ሆሳዕና(FEAST OF PALM SUNDAY)❖❖

ሆሳዕና ማለት መድኃኒት አንድም አኹን አድን ማለት ነው።ይህ በዓለ የሰሙነ ሕማማት የመጀመርያ ቀን ነው፤ማለትም መነሻ ማለት ነው። Holy Week begins with Palm Sunday(ቅዱሱ ሳምንት(ሰሙነ ሕማማት የሚጀመረው በሆሳዕና) እንዲል።በዚህ በዓል ላይ የምናገኘው ክዋኔ አብዛኛዋቹ ሊቃውንትት እንዳተቱት በነብዩ ቅዱስ ዘካርያስ ከተነገረው ትንቢት ነው።"ለጽዮን ልጅ እነኾ የዋህ ንጉሥሽ በአህያይቱና በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሏት።ዘካ ፱፥፱ በማለት ገልጿል።

የሆሳዕና በዓል ከዘጠኙ ዐበይት የጌታችን በዓላት መካከል አንዱ ነው።

ይህ በዓል ከተፈጸመበት ድርጊት የተነሣ በአብዛኛዎቹ የጥንት አብያተ ክርስቲያን(PALM SUNDAY) ተብሎ ይጠራል።PALM ማለት የዘንባባ ዝንጣፊ ማለት ነው፤በዓሉ የሚከወነው በዕለት እሑድ መኾኑን ለመግለጥ(SUNDAY) የሚለውን ቃል እንጠቀማለን።በዐለ ሆሳዕና መሠረታዊ ከሚባሉ በዓላት መካከል ስለኾነ በኹሉም ዘንድ በደማቅ ይከበራል።የዘንባባዋ እሑድ(PALM SUNDAY) Palm Sunday is a Christian moveable feast that

falls on the Sunday before Easter . The feast commemorates Jesus

'triumphal entry into Jerusalem , an event mentioned in each of the four canonical Gospels.(የዘንባባው እሑድ ከትንሣኤው በፊት ባለው እሑድ ላይ የሚውል ተንቀሳቃሽ በዓል ነው።ይህ በዓል የሚያስታውሰን በአራቱም ወንጌላት የተዘገበውን የጌታችንን ወደ ኢየሩሳሌም ገብቶ ድል ማድረጉን ነው።ጌታችን የዚህን በዓል ኹኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ብሎ ነው የገለጠልን፦"ጌታችን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦ ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተፋጌ በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ኺለቱን ላከ።እንዲህም አላቸው፤ "በፊታችሁ ወደ አለችሁ መንደር ሂዱ ያን ጊዜ የታሰረች አህያ ከውርንጫውዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ፍቱና አምጡልኝ።ምን ታደርጋላችሁ? የሚላችሁ ቢኖርም ጌታቸው ይሻቸዋል በሉ፥ያንጊዜ ይሰዱአቸኃል።" በማለት አስተምሯል ማቴ ፳፩፥፩-፫ ።ይህንን ትዕዛዝ አምላካችን ያቀረበው ወደ ቤተ ፋጌ ከደብረ ዘይት አቅራብያ ወደ ሚገኘው ስፍራ ቀርቦ ነው።የእስክንድርያው ሊቅ ኦሪገን ቤተ ፋጌን(the house of cheek) ይህ የሚያመለክተው አምላካችን ክርስቶስ ኢየሩሳሌም ወደተባልነው ወደ እኛ የሚገባው በወንጌል ላይ እንደተጻፈ ጉንጫችንን ስንሰጥ ነው።ቀኝህን ለሚመታ ግራህን ስጥ እንዳለው በተቀደሰው ጉንጫችን አማካኝነት እግዚአብሔር ወደ እኛ እንደሚገባ ለማስረዳት መጽሐፍ ወደ ቤተ ፋጌ ቀርቦ በማለት የታሪኩን ክዋኔ ዘገበልን።ይህቺ ቤተ ፋጌ የበለስ ቤት ስለኾነች በለስ የተባለችውን የቤተክርስቲያንን አንድነትን የምታሳይ መኾኗን እንገነዘባለን።ይህቺ ስፍራ የድሆች መንደር በመኾንም ትታወቃለች።አምላካችን እግዚአብሔር ደሀ የተባልነውን እኛን ወደ ቀደመ ክብር ሊመልሰን እንደመጣ እንረዳ ዘንድ በቦታዋ የእኛን ድህነት ገልጦ፤በቦታዋ ላይ በቆመው በእርሱ አማካኝነት ወደ ሀብት ከፍ እንደምንል ለማስረዳት በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያት አዘዛቸው። ደብረ ዘይት ደግሞ ራሱ ክርስቶስን የምታሳይ ናት።ቅዱስ አምብሮስ እንዳለው የደብረ ዘይት ተራራ የተባለው ከክርስቶስ በቀር ማን ነው? በማለት እንደጠየቀው።እርሱ የሕይወታችን መጀመርያና መጨረሻ ነው።ወደ እርሱ ማለትም ወደ ደብረ ዘይት ስንወጣ አብረነው ኢየሩሳሌም እንገባለን ማለት ነው።

❖❖❖

ጌታችን ጌታ ነውና ማንኛውንም ነገር ይቀድሳል እንጂ እርሱ በማንም አይቀደስም።እኛ እርሱን የምናመሰግነው ክብር ይግባውና የሚጎለው ነገር ስላለ ሳይኾን እኛ እንመሰገን ዘንድ ነው።አህያ በብሉይ ኪዳን የተናቀችና ለመሥዋዕት የማትቀርብ እንስሳ ናት።እግዚአብሔር አትብሏቸው ካላቸው እንስሳት መካከል አንዷ አህያ ናት።ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህቺን አህያ ከአዳም ውድቀት በኃላ ያለውን ሰብአዊነት የምታሳይ ናት(Representatives of humanity)።ይህቺ እንስሳ ትልቅ ክብደት ያላት፣ሰዎችንም ይኹን ቁሳቁሶችን በመሸከም የምትታወቅ ናት።ክርስቶስ በዚህች አህያ ላይ መቀመጡ በኃጢአታችን ምክንያት ያገኘንን የባሕርይ ጉስቁልና(failure of nature) አጥፍቶልን በደሙ ቀድሶን በፍቅሩ ወደ ራሱ ስቦን ይነግሥብን ዘንድ ነው።ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያም አህያይቱን ሰዎች በክፋትና በኃጢአታቸው ምክንያት የሚያገኛቸውን የተዋረደ ማንነት መኾኑን ገልጿል።ቅዱስ ዳዊትም ያለው ቃል ተፈጸመ ሰብእሰ እንዘ ክቡር ውእቱ እያእመረ ወኮነ ከመ እንስሳ ዘገዳም ወተመሰሎሙ(ሰው ግን ክቡር ነበር ነገር ግን አላወቀም፤የምድረ በዳ እንስሳትንም ኾነ መሰላቸውምም።) እንዲል ከሕግ ማፈገጥ የሚያመጣብን ክብ ነገር ከዚህም የባሰ ነው።ክርስቶስ በዚህች አህያ ላይ መቀመጡ ምንም ኀጥእ ብንኾንም ወደ ንስሓ ከመጣንና ከታሰርንበት የኃጢአት እስራት በአባቶቻችን ጸሎት ምክንያት ከተፈታን ንጉሥ ክርስቶስ የንግሥናው ዙፋን አድርጎን ይቀመጥብናል።አህያይቱና ውርጫዋ የአይሁድና የአሕዛብ ምሳሌ(representatives of Jews and Gentile) ተደርገው ይተረጎማሉ።ክርስቶስ ሰው ኾኖ የመጣው ኹላችንንም ሊያድነንና ወደራሱ እቅፍ ሊስበን ነው።ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ነበር ያለው"እኔ የተናቅኹ ነኝ፥አላወቅሁምም በአንተ ዘንድ እንደ እንስሳ ኾንኹ።እኔ ግን ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ ቀኝ እጄንም ያዝኽኝ።በአንተ ምክር መራኽኝ።"መዝ ፸፪፥፳፪ በማለት እግዚአብሔር ከውርደቱ እንዳነሣውና በምክሩም እንዲሔድ እንዳደረገው አስገነዘበን።ከመንደር የመጣችው ውርንጫይቱ uncivilized thought of atheists(ያልሰለጠነ እግዚአብሔር የለም የሚል ዕሳቤ) የምታሳይ ናት።ሊቁ ኦሪገንም አህያይቱን የአይሁድ ማኅበር(Jews syndicate) የምታሳይ ናት ይላል፤ውርጫይቱ ደግሞ ዕውራን የኾኑ አዲስ የተወለዱ አሕዛብን(Newborn Gentile) የሚያመለክት ነው ይልና ወደኢየሩሳሌም መግቢያ በሩን እንደከፈተላቸውና በተጨማሪም ጌታ የተቀመጠባቸው ሸክማቸውን ሊያቀልላቸው እንደኾነና ኹሉንም አንድ አድርግ ለማገናኘት መኾኑን አስረድቷል።ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም the colt meant the church ውርጫይቱ ቤተክርስቲያን ናት በማለት የቤተክርስቲያንን ውበት አዲስ በተወለደችው ውርጫ በኩል ይገልጽልናል።በእርግጥ ከክርስቶስ ነግሦባት ምሥጢረ ሥላሴ ደምቆ ይሰበክባት ዘንድ ሦስት ጊዜ ቤተመቅደሱን የዞረባት አዲሲቶ ግልገል እናታችን ቤተክርስቲያንን ትመስላለች።ሊቁ አባ ጀሮም ደግሞ ጌታ ኹለቱን ደቀ መዛሙር የላከው አነሰዱን ወደ ግዙራኑ አይኹድ ሲኾን ሌላኛውን ወደቁልፋኑ አሕዛብ መላኩን ለማመልከት ነው ይላል።ቅዱስ ሒላሪም ተመሳሳይ በኾነ ምሥጢር ኹለቱ ደቀመዛሙርት የተላኩት በኹለት ወገን አሕዛብ ወደ ኾኑት ነው።አንደኝቹ ሳምራዊያን ናቸው በተወሰነ ደረጃ እግዚአብሔርን ያውቃሉ እነዚህ በአህያይቱ(donkey) ሲመሰሉ ፈጽመው እግዚአብሔርን የማያውቁት ደግሞ በውርጫይቱ ይመሰላሉ በማለት ያትታል። አህያይቱ የኦሪት ውርጫይቱ ደግሞ የወንጌል ምሳሌም ተደርገው ይብራራሉ።ሽክም የለመደችው አህያ በቤተእስራኤል ስትመሰል ሽክም ያልለመደችው ውርጫ ደግሞ በአሕዛብ ይመሰላሉ።ከዚህ ኹሉ በላይ የሚያስደንቀው በአህያ ላይ መስቀለ ክርስቶስ( Christ's cross)መኖሩ ነው።ይህቺ አህያ በእርግጥም የአሕዛብ ብቻ ሳይኾን የክርስቶሰ ተከታ


ይ(followers of Christ) የምንባል እኛን ክርስቲያኖችን የምትመስል ናት ብንል ምን ይደንቅ! የክርስቶስ መስቀል በልቦናው ከታተመበትና በሕሊናው ከተቀረጸበት በቀር የክርስቶስ ዙፋን ማን ሊኾን ኖራልና ነው!! ይህቺ አህያ የትሕትና ምሳሌም ናት።እግዚአብሔር በትሑታን ልብ እንደሚቀመጥ የሚያመለክት ምሥጢር አላትና።አዳምና ልጆቹ ከትሕትና መንገድ ሲወጡና ወደ ትዕቢት ሲወርዱ ከእግዚአብሔር የንግሥና ዙፋንነት ወደ ዲያብልስ ቤትነት ተሸጋገሩ።በዚህ ምክንያት ወደ ቀደመ የንግሥና ወንበርነት እኛን ከፍ አድርጎን ንጉሥ ክርስቶስ ሊያበራብን በአህያይቱ ላይ ተቀመጠ።ከዚህ በተጨማሪ በአሕያይቱ ላይ ተቀምጦ የጎደሉንን ኹለት ነገሮች እነርሱም(love of God and love of man) ሊሞላልን ኹለቱን ምዕራፍ በአህያይቱ ላይ ተቀመጠ፤ኹለት ነገር ጓሏችሁ ነበር ሞላሁላችሁ ሲል።

❖❖❖

ይህቺ አህያ በዛሬው ዕለት ተደርጎ የማያውቅ ነገር ተደረገላት።በላዯ ልብስ ሲደረግላት እግሮቿን ቆሻሻ እንዳይነካው ደግሞ የዘንባባ ዝንጣፊና ልብስ ተነጠፈላት።ያን ኹሉ መከራ እናደርስባት የነበረውን ወዲያው ዘነጋነውና ታላቅ ክብር አደረግንላት።ልብሶቻቸውን አውልቀው ለክብር ንጉሥ አነጠፉለት ምክንያቱም እውነተኛ የጽድቅ ልብስ እርሱ ነውና፤እነርሱም በእርሱ የጽድቅ ልብስ ተጠቅልለው በውስጡም ተሸሽገው ይኖራሉና።ልብሶቻቸውን አውልቀው ሲያነጥፉለት እርሱ ደግሞ ልብሳቸውን ይለውጥላቸው ነበር ወደራሱም ያስጠጋቸው ነበር፤ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ኤርሚያስ ፶፪፥፴፫"በወህኒም ውስጥ ለብሶት የነበረውን ልብስ ለወጠለት።" በማለት በኃጢአት ወህኒ ውስጥ ገብተን ያለነውን እኛን የለብስነውን ልብስ ስናወልቅለት እርሱ ደግሞ የክብርን ልብስ በምሥጢር ያለብሰናል።ቤተክርስቲያን ምዕመናን ልብሷን ለክርስቶስ ክብር ብላ ካወለቀች በኃላ የጌታዋን ጣፋጭ የኾነ ቃል ታደምጣለች።እርሱም እንዲህ ይላል፦"ሙሽሪት ኾይ ከከንፈርሽ የማር ወለላ ይንጠባጠባል፤ከምላስሽም በታች ማርና ወተት አለ፥የልብስሽንም መዓዛ እንደ ዕጣን፥መዓዛ ነው።"ይህ የሚያስረዳን ከልባችን ኾነን ለንጉሠ ሰማይ ወምድር የምናቀርብለት ልብስ እንደ ዕጣን መዓዛ ያማረ ኾኖ በሙሽራው ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል።እርሷ ደግሞ መልሳ ለሙሽራዋ እንዲህ ትለዋለች፦"ነፍሴም በእግዚአብሔር ሐሜት ታደርጋለች።ሽልማትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥በጌጥ ሽልማቷም እንዳጌጠች ሙሽራ፥የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥የደስታንም መጎናጸፊያ ደርቦልኛልና።" ኢሳ ፷፩፥፲ ላይ ሙሽራው ሙሽሪት ቤተክርስቲያንን የሚያለብሳትን የድኅነት ልብስ ገለጸልን።በዚህች አህያ ላይ ንጉሥ ይቀመጥባታል፤ይህ ንጉሥ ብርህትና ምንም የማትቆረቁር ሕግን ለሕዝብ ኹሉ የሚያድል መኾኑን ለማጠየቅ በአህያይቱ ላይ ልብሳቸውን ደረቡባት።ይህንን ልብስ አዎልቀው በአህያይቱ ላይ ማድረጋቸው ፍጹም ጊዜ ደስ መሰኘታቸውን ለምግለጥ ነው፤ይህን ሀሳባቸውን ያወቀላቸው አምላክም የደስታንና የማዳንን ልብስ አለበሳቸው።በሌላ መንገድ ደግሞ አህያይቱ የእኛ ምሳሌ ስለኾነች ልብስ ማድረጋችን የንስሓን ልብስ አልብሰኽን ተቀመጥብን ለማለት ነው።ልባሳቸውን ማንጠፋቸው አማናዊው ልብሳችን አንተ ነህ ሲሉት ነው።አንድም ከጸጋ ተራቁቶ የነበረውን የሰውን ልጅ የቀደመውን የጸጋ ልብስ የሚያለብሰውና ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያድለው ንጉሥ መኾኑ ለመግለጥ ልብሳቸውን አነጠፉለት።ቅዱስ አግናጢዎስ እንዲህ ይል ነበር፦ This means that the

person who has left his sinful life is led to the Gospels, and is clothed as if in apostolic

vestments, in the most detailed and refined knowledge of Christ and Hiscommandments.(ይህ ማለት የኃጢአተኝነቱን ሕይወት ሲተወው ወደ ወንጌል ይሄዳል፤ሐዋርያዊ በኾነ መልኩ የበዐል ልብርን ይለብሳል፤በጣም በተብራራና በተጣራ ኹኔታ ክርስቶስንና ሕጉን ያውቃል።) ልብስን መልበስ ማለት ክርስቶስን ወደ ማወቅ ልዕልና መውጣትና ሕጉን ወደ መጠበቅ ማደግ ነው።አባ ጀሮምም ኹለቱ ደቀመዛሙርት በአህያይቱ ላይ ያስቀመጡት ልብስ እውነቸኛ ትምህርትን(teaching of righteousness)፣የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጓሜ(interpretation of holy book) እና የቤተክርስቲያንን እውነት(truth of church) ያሳያል ይልና።ነፍሳችን በእነዚህ ካላጌጠችና ከልተጠቀለለች ክርስቶስ ሊቀመጥባት አይችልም በማለት ግሩም የኾነ ምሥጢር አቅርቦልናል።ይህ የሆሳዕና በዓል ከእነዚህ ድንቅ ክዋኔዋቹ ተለይቶ ፈጽሞ ሊያምርና ሊደምቅ አይችልም።

Report Page