Capital

Capital

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

ከህዳሴ ግድብ ከ3 እጥፍ በላይ ወጪ የሚጠይቅ የብረት ማእድን ማቀነባበሪያ ለመገንባት የተያዘ እቅድ!

የብረታ ብረት ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት (ብኢልኢ) የቀጣዩን የአገሪቱን የብረት ፍላጎት እድገት እና የወቅቱን የግብአት ችግር ከመሰረቱ ያሻሽላል ያለውን የብረት ማእድን ማቀነባበሪያ ለመገንባት የሚያስችል ጥናት መስራቱን አስታውቋል፡፡

በሁለት ምእራፎች ለሚገነባው ማቀነባበሪያ 14.7 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተገመተ ሲሆን ይህም የህዳሴ ግድብን ለመገንባት ይወጣል ተብሎ ከሚገመተው ከ3 እጥፍ በላይ መሆኑ ታቀወቋል፡፡

በብኢልኢ የእቅድ እና መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጥላሁን አባይ ለካፒታል እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ በመንግስት ግል አጋርነት መርህ እንዲከወን የሚጠበቅ ሲሆን መንግስት የ20 በመቶ ድርሻ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡

ለፕሮጀክቱ የመነሻ ጥናት በብሪታንያው MCI Group የተሰራ ሲሆን የቅድመ አዋጭነቱ በቻይና ተከናውኗል ብለዋል፡፡

በዚህ አምስት አመት የአዋጭነት እና የመጀመሪያ ምእራፍ ግንባታ ለማከናወን የታቀደ ሲሆን፡፡ ለመጀመሪያ ምእራፍ ግንባታው 7.05 ቢሊየን ዶላር ወጪ እንደሚደረግ አቶ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

ይህ በረጅም ግዜ ለብረታብረት እና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ማነቆ የሆነውን የጥሬ እቃ እጥረትን ለመቅረፍ ታሳቢ ያደረገው ፕሮጀክት ሁሉን አቀፍ የሆነ እድገትን ከማረጋገጥ አንፃር መሰረታዊ ነው ተብሎለታል፡፡

ለማቀነባበር የሚሆን የብረት ማእድን ከአገር ውስጥ እና ከውጭ በማስገባት እንደሚጠቀምም ታሳቢ ተደርጓል፡፡

የብረት ማእድን ምርት ለመጀመር በተለይ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች እንቅስቃሴ መኖሩ የታወቀ ሲሆን በዘርፉ ልማት ሶስት የሚሆኑ ፈቃዶች በማእድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር በኩል መሰጠቱ ታውቋል፡፡

የመጀመሪያ ምእራፍ ግንባታው ስራ ሲጀምር በአመት 5 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የማምረት አቅም እንደሚኖረው ይጠበቃል ያሉት አቶ ጥላሁን በ10 አመት ጊዜ ውስጥ ማቀነባበሪያው ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ታቅዷል፡፡

መሰል የብረት ማቀነባበሪያዎች ለአገራት የኢኮኖሚ እድገት መሰረታዊ መሆኑ በሌሎች እንደ ቻይና እና ኮርያ ታይቷል የሚሉት አቶ ጥላሁን፡፡ በዘርፉ በአፍሪካ ጥሩ ውጤት እያገኘች ያለችው ግብፅ ለዚህ ጥሩ ማሳያ እደሆነች አክለዋል፡፡

ማቀነባበሪያውን ለመገንባት ማእድን ሊኖር የግድ አይደለም የሚሉት ዳይሬክተሩ፤ ቻይና ማእድኑ ሳይኖት በብረት ምርት በአለም ቀዳሚ መሆኗ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ ያብራራሉ፡፡

ግብፅ በገነባችው ማቀነባበሪያ በአመት 7.8 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ጥሬ ብረት/ crud steel እንደምታመርት የታወቀ ሲሆን ለግብአት የሚሆነውን 5.6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የብረት ማእድን ከውጭ 1.5 ሚሊየን ሜትሪክ ቶኑን ደግሞ ከማእድን ማውጫዋ ትጠቀማለች፡፡

ኢንስቲትዩቱ ለብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንደስትሪ ዘርፉ የግብአት ማነቆ የሆነውን ችግር በተለያየ ደረጃ የመቅረፍ እቅድ የነደፈ ሲሆን፡፡

በአጭር ጊዜ አምራቾች የውጭ ምንዛሬ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ከባንኮች የሚያገኙበትን መንገድ ከሚለከታቸው አካላት እያፈላለገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

እንደ አቶ ጥላሁን የብረት ዘርፉ እንደ አገር ስተራቴጂያዊ ቢሆንም ከባንኮች ከመመሪያ ውጭ ባፈነገጠ መልኩ ፍትሃዊ የውጭ ምንዛሬ አሰጣጥ ባለመኖሩ የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ከብሄራዊ ባንክ ባለፈ በባንክ መተማመኛ ሰነድ / LC ፈቃድ ላይ ድርሻ እንዲኖረው ተጠይቋል፡፡

በመካከለኛ ግዜ እቅድ ደግሞ ጥሬ ብረት እና የብረት ማእድን እያስገቡ የሚያመርቱ የውጭ አምራቾችን ለመሳብ እየተሰራ ሲሆን፡፡

በዚህ ረገድ ፖስኮ የተባለ የደቡብ ኮርያ እንዲሁም በዘርፉ ከሚጠሩ ግንባር ቀደም ኩባንያዎች በቀዳሚ ተርታ የሚጠቀስ አምራች ለመግባት ሂደት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

Report Page