bu sl fr usd የሞጣ ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት

bu sl fr usd የሞጣ ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት

Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሞጣ ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2013 በጀት አመት እቅድ መሰረት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎች ማለትም፡-

ሎት 1/ምድብ/ አንድ የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያዎችን ለመግዛት
ሎት 2/ምድብ/ ሁለት ኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ እቃዎችን ለመግዛት
ሎት 3/ምድብ/ ሶስት ደግሞ ባለ 6 እና ባለ 12 ሜትር ኮንቴነሮትን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለበትና ማስረጃ ማቅረብ መሆን አለበት፡፡
  2. ተወዳዳሪው በተራ ቁጥር አንድ የተዘረሩትን ማስረጃዎች ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ሲፒኦ ብሎ በመለየት በፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ዝርዝር እቃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ፎረም ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ/ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6.  ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ቢሮ ቁጥር 03 በማምጣት ማስገባት ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለበት ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  7. አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ከ5 ቀናት በኋላ ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመያዝ የአሸነፋቸውን እቃዎች ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  8.  ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጐ በእለቱ ከጠዋቱ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስራ ሂደቱ ስልክ ቁጥር 0586611971 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሞጣ ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

__________________

Posted:በኩር መስከረም 18፣ 2013

Deadline:በ16ኛው ቀን 3፡00

__________________
© walia tender


Report Page