BBC

BBC


ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ማን ነበር ?


• ነሐሴ 22/1960 ዓ.ም ከኤርትራውያን ቤተሰቦቹ በቢሾፍቱ ከተማ ነበር ተወልዶ ያደገው።


• ቤተሰቦቹ መነሻቸው ኤርትራ ሲሆን ከኤርትራ ድባርዋ ወደ መሐል አገር በመምጣት ኑሯቸውን ቢሾፍቱ ላይ አደላድለው ለዓመታት በመኖር ልጆችን አፍርተዋል።


• ተስፋዬ ከፍተኛ የሆነ የሥነ ጽሁፍ ፍቅርና ዝንባሌ ስለነበረው ከወጣት ነት ዘመኑ አንስቶ ከበርካታ ታዋቂ የኢትዮጵያ ፀሐፊያን ጋር የቀረበ ግንኙነት ነበረው።


• በደርግ ዘመን ማብቂያ አካባቢ ወደ ጦር ሠራዊቱ ተመልምሎ ሥልጠና ከወሰደ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ወታደራዊው መንግሥት ወድቆ ከኢህአዴግ ጋር ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በጋዜጠኝነት ሲያገለግል ቆይቷል።


• ታዋቂዎቹን ዕለታዊ የመንግሥት ጋዜጦችን የሚያሳትመው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ አገልግሏል።


• ከኢህአዴግ ፓርቲ ጋር ጥብቅ ቁርኝት የነበረው "እፎይታ" መጽሔትን መርቷል።


• ተስፋዬ በኢትዮጵያ ሳለ ከጋዜጠኝነት ሙያው ጎን ለጎን መጽሐፍቶችንም አሳትሟል፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር በነበረው አለመግባባት ኢትዮጵያን ጥሎ ከወጣ በኋላ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኔዘርላንድስ እና ሌሎችም አገራት ውስጥ ኗሯል።


• የጋዜጠኝነት ሥራውን ካቆመ በኋላ አስከ ህይወቱ ፍጻሜ ድረስ የሙሉ ጊዜ ፀሐፊ በመሆን ከስምንት በላይ ሥራዎችን ለአንባቢያን አድርሷል።


• ከ8 በላይ ስራዎችን በአማርኛ ያሳተመ ሲሆን በአንባቢያን ዘንድ በስፋት ያስተዋወቀው "የቡርቃ ዝምታ" የተሰኘው ረዥም ልብ ወለዱ ነው፡ ይህ የልብወለድ መጽሐፉ በበርካታ የአማርኛ ልብወለድ አንባቢያን ዘንድ ነቀፌታን አሰንዝሮበታል።


• ተስፋዬ የግል ማስታወሻዎችን፣ ልብወለድ፣ አጫጭር ልብወለድ እንዲሁም ወጎችን በመጻፍ አድናቆትን አትርፏል።


• የትግል ጅማሬ አስከ ኢህአዴግ አዲስ አበባ መግባት ድረስ ያለውን ዋና ዋና ታሪክና ገድል የሚተርከውን ተከታታይ ቅጽ ያለውን "ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ" መጽሐፍትንም በማሳተም ይታወቃል።


• ተስፋዬ በጋዜጠኝነቱና በሥነ ጽሁፉ ዘርፍ የገዢው ኢህአዴግ ዋነኛ ሰው በመሆን የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ እሱ እንደሚለው ከአገሪቱ ዋነኛ ፖለቲከኞች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ኢትዮጵያን ለቅቆ ለመሰደድ በቅቷል።


• ከአገር ከወጣ በኋላ ብዙ መነጋገሪያ የሆኑ የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግና የባለሥልጣናቱ የውስጥ ምስጢር የሆኑ ጉዳዮችን የያዙትን "የጋዜጠኛው ማስታወሻ" እና "የደራሲው ማስታወሻ" የተሰኙ መጽሐፎችን ለንባብ አብቅቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Report Page