AFP

AFP


#IOM

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) የኢትዮጵያ ኃላፊ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ "ያልተፈቀደ ቃለ መጠይቆችን" አድርገዋል በሚል የመንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ መደረጋቸውን AFP ዘገበ።

ኃላፊዋ ማውሪን አቺየንግ ያልተፈቀደ በተባለው ቃለ መጠይቅ ለትግራይ ኃይሎች ርህራሄ አላቸው ባሏቸው የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ጎን ገሸሽ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

ይህንንም አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃለ አቀባይ ቢልለኔ ስዩም "የተባበሩት መንግሥታት ሥርዓት ከሽብርተኛው ቡድን ህወሓት ጋር ባለው ግንኙነት ተቋማዊ አድሏዊነትን መከተሉን በግልፅ በመናገራቸው ማውሪን አቺየንግ ላይ የተጣለው አስተደዳራዊ እረፍት በጣም የሚረብሽ ነው" ብለዋል።

አክለውም "በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በከፍተኛ የሥልጣን እርከኖች ያለው ውስጣዊ እና የውጭ ተፅእኖ ፓለቲካ በጥልቀት መመርመር እንዳለበት" በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

የኃላፊዋ ከሥራ ኃላፊነታቸው መነሳት በያዝነው ሳምንት ሰኞ በተፃፈና የዜና ወኪሉ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በተመለከተው ደብዳቤ የተረጋጋጠ ሲሆን በበለጠ የእርዳታ ሥራውን እንደሚያዳክመውም ተጠቅሷል።

በቅርቡ ኢትዮጵያ "በውስጥ ጉዳዮቼ ጣልቃ ገብተዋል" ያለቻቸውን ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞችም መባረር ድርጅቱ ለሰብአዊ እርዳታ በሚሰጠው ምላሽ ላይ እክል እንደሆነበትም ሰፍሯል።

ባለፈው ሳምንት ማውሪን አቺየንግና እና ሌላ ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኛ የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ላይ የሚያደርገውን ዘመቻ በመደገፍ በርካታ መጣጥፎችን ለሚፅፈው ጄፍ ፒርስ ረዘም ያለ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል።

በቃለ መጠይቁ ላይ እንደሚሰማው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ኃላፊ ማውሪን ጦርነቱ ከተነሳ በኋላ አዲስ አበባ የገቡ የተባበሩት መንግሥታት የሥራ ባልደረቦቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ በመተቸት መሬት ላይ ያሉ የድርጅቱ ተወካዮችን አግልለዋል ብለዋል።

ህወሓትንም "ቆሻሻ" እና "ጨካኝ" በማለትም ሲሳደቡ ይሰማል።

በአንድ ወቅትም ህወሓት ከሳዑዲ አረቢያ የተባረሩ የትግራይ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ አሲረዋል በማለትም ሲከሱ ይሰማል።

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የነበሩና መውጪያ አጥተው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ ጥያቄ እንደቀረበላቸውና ሩዋንዳም እንዲላኩ የተፈለገው ለሌላ አላማ እንደሆነ ሲናገሩም ይሰማል።

"እናም ከዚያ የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ ከሩዋንዳ እንደሚጀመር አታውቅም ማለት ቆሻሻ ነው" ይላሉ።

ኃላፊዋ በጭራሽ ወደ ትግራይም እንደማይመለሱ ቃል ሲገቡም ይሰማል።

ባለፈው ሳምንት ኤኤፍፒ በተመለከተውና ለሥራ ባልደረቦቻቸው በታየ የውስጥ ማስታወሻ፣ ኃላፊዋ በበኩላቸው "በጥልቅ ተረብሻለሁ እናም አዝኛለሁ" ካሉም በኋላ "በስውር እንደተቀዳና ተመርጦ አርትፆት እንደተደረገበት" ተናግረዋል።

ነገር ግን በቃለ መጠይቁ ወቅት በበርካታ ነጥቦች ላይ ተሳታፊዎቹ እየተቀዳ መሆኑን በግልፅ ሲወያዩም ይሰማል።

ሰኞ እለት የአይኦኤም ዋና ዳይሬክተር አንቶኒዮ ቪቶሪኖ የኃላፊዋን አስተያየቶች አስመልክቶ ደብዳቤ ፅፈዋል።

"በድምፁ ላይ በድርጅቱ አባል የተሰጡት አስተያየቶች ከአይኦኤም መርሆች እና እሴቶች ጋር አይዛመዱም፣ በምንም መልኩ የድርጅቱ አቋም እንደተገለጸ ተደርጎ መታየት የለበትም" ብለዋል።

ደብዳቤው ማውሪን አቺየንግን በስም የማይጠቅስ ቢሆንም ምርመራው እስኪካሄድ ድረስ ወዲያውኑ እንደተጠሩ እና የአስተዳደር እረፍት ያደርጋሉ ተብሏል።

ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከተከሰተው ቀውስ ጋር ተያይዞ በወገንተኝነትና እንዲሁም ለብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ደቅነዋል ያለቻቸውን የተመድ ሰባት ሠራተኞች ከአገር እንዲወጡ ማድረጓ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ/AFP

@tikvahethiopia


Report Page