BBC

BBC

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

የእስራኤሉ ወታደር የፍልስጤማዊው አንገት ላይ መቆሙ ቁጣን ቀሰቀሰ

REUTERS

የእስራኤል ጦር አባል ለተቃውሞ የወጡት ፍልስጤማዊ አዛውንት አንገትን በጉልበቱ አፍኖ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ከወጣ በኋላ ቁጣን ቀስቅሷል።

ካሂሪ ሃኑን የተባሉት ዝነኛው ተቃዋሚ አዛውንት እጆቻቸው ወደኋላ ታስሮ፤ ፊታቸው ከመሬት ጋር ተጣብቆ የእስራኤል ወታደር አንገታቸው ላይ በጉልበቱ ቆሞ የሚያሳየው ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል።

ምስሉ የተቀረጸው ትናንት ፍልስጤማውያን በዌስት ባንክ ለተቃውሞ በወጡበት ወቅት ነው።

ወታደሩ በጉልበቱ የካሂሪ ሃኑን አንገት ላይ ለ50 ሰከንዶች ያክል ተጭኖ ቆይቷል። ይህም በፍልስጤማውያን ዘንድ ሌላ ታቃውሞን ቀስቅሷል።

የእስራኤል ጦር ግን የጦር አባላቱ የነበረውን ሁኔታ ለመቆጣጠር ተመጣጣኝ እርምጃ ነው የወሰዱት ብሏል።

ተንቀሳቃሽ ምስሉም የግጭቱን ሙሉ ምስል አያሳይም፤ በጦር አባላቱ ላይ ሲደርስ የነበረውን ጥቃትም አያስመለክትም ብሏል።

ጦሩ ጨምሮ ወደ 200 ሰዎች ግጭት በተስተዋለበት የተቃውሞ ስልፍ ላይ መሳተፋቸውን እና በጦሩ አባላት ላይ ድንጋይ መወርወሩን አሳውቋል።

የእስራኤል ጦር በመግለጫው ካሂሪ ሃኑን በእስራኤል ጦር አባሉ ላይ ተደጋጋሚ ትንኮሳ መፈጸማቸውን እና አባላቱ በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት ተባባሪ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እርምጃው እንዲወሰድባቸው ግድ መሆኑን አብራርቷል።

REUTERS

ካሂሪ ሃኑን ጥቃቱ ከደረሰባቸው በኋላ ለአንድ የእስራኤል ጋዜጣ “በቁጥር አስተኛ የሆንን በእድሜ የገፋን አዛውንቶች ወታደሮቹ ጉዳት አያደርሱብንም ብለን ተሰባስበን ለተቃውሞ ወጣን። ልክ እንደ ሌባ ጉዳት አደረሱብን” ሲሉ ተናግረዋል።

ካሂሪ ሃኑን ክስተቱን ከአሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ጋር አዛምደውታል።

ግንቦት ወር ላይ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ነጭ የፖሊስ አባል በጉልበቱ አንገቱ ላይ ለረዥም ደቂቃዎች ከቆመ በኋላ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

“ያን አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ። አፍኖኝ ነበር” ብለዋል ካሂሪ ሃኑን።

Report Page