#BBC

#BBC


ኒው ዚላንድ!

በሽታውን በቁጥጥር ሥር ማዋሏን በተናገረችው ኒው ዚላንድ ሁለት (2) ሰዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል። ሁለቱም ከዩኬ ወደ ኒው ዚላንድ የገቡ መሆናቸውም ተገልጿል።

በ30ዎቹ እና በ40ዎቹ እድሜ ክልል የሚገኙት ሴቶች ወደ ኒው ዚላንድ እንዲገቡ የተፈቀደው በሞት አፋፍ ላይ የነበረ ወላጃቸውን ለማየት ጥያቄ ስላቀረቡ ነው ተብሏል።

ግለሰቦቹ ሰኔ 7 ኒው ዚላንድ እንደገቡ ወደ ለይቶ ማቆያ ተወስደዋል። የአገሪቱ የጤና ሚንስትር ዋና ኃላፊ ዶ/ር አሽሊ ብሉሚፊልድ እንዳሉት፤ አንደኛዋ ሰው መጠነኛ ምልክት ታሳይ ነበር።

ሰኔ 12/2020 ወላጃቸውን ለማየት ጥያቄ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፤ የዛኑ ቀን ወላጃቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ዋና ኃላፊው እንዳሉትም ግለሰቦቹ ሰኔ 13 በግል መኪና፣ ከማንም ጋር ሳይነካኩ የወላጃቸው ቀብር ላይ እንዲገኙ ተደርጓል።

አብሯቸው የነበረ ዘመዳቸው ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገባ ተደርጓል። “የተሰጣቸውን መመሪያ ስለተገበሩ ሌላ ሰው በክለዋል ብዬ አላስብም” ብለዋል ዶ/ር አሽሊ።

ምንጭ፦ #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia


Report Page