BBC

BBC

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

አንድ አዲስ የተወለደ ቻይናዊ ጨቅላ ከተወለደ ከ30 ሰዓት በኋላ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘበት የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ፤ ይህም ህጻኑን በበሽታው የተያዘ በዕድሜ ትንሹ ሰው ያደርገዋል።

ህጻኑ የተወለደው የመሽታው መነሻ ናት ተብላ በምትታመነው ዉሃን ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ እንደሆነም ተነግሯል።

የህፃኑ እናት ከመውለዷ በፊት በተደረገላት ምርመራ የበሽታው ቫይረስ እንዳለባት የታወቀ ቢሆንም በሽታው እንዴት ወደ ህጻኑ እንተላለፈ ግን ግልጽ አይደለም።

እስካሁን ከ28 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ባጠቃው በዚህ ቫይረስ 563 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በበሽታው የተያዙ ህጻናት ቁጥር ግን ውስን እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የመንግሥት የዜና ተቋም የሆነው ዢንዋ ነው አዲስ የተወለደው ህጻን ላይ ቫይረሱ ስለመገኘቱ የዘገበው፤ አክሎም በደህና ሁኔታ ላይ የሚገኘውህጻኑ 3.2 ኪሎ ግራም እንደሚመዝንና ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ገልጿል።

የህጻኑ በማህጸን ውስጥ እያለ ቫይረሱ ከእናቱ ተላልፎበት ሊሆን እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።

"ይህም የኮሮናቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ እድል እንዳለው ተረድተን ተገቢውን ትኩረት እንድንሰጥ ያደርገናል" ሲሉ በዉሃን የህጻናት ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዜንግ ሊንግኮንግ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ነገር ግን ህጻኑ ምናልባትም ከተወለደ በኋላ ከእናቱ ጋር በሚኖር የቅርብ ንክኪ ሳቢያ በቫይረሱ ተይዞ ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል።

"ህጻኑ ቫይረሱ መደበኛ በሆነው የበሽታ መተላለፊያ መንገድ ሊያገኘው ይችላል። ይህም እናቱ በምትስል ጊዜ በትንፋሽ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው" ያሉት ደግሞ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ኤፒዴሞሎጂስት የሆኑት ስቴፈን ሞርስ ናቸው።

የበሽታው ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ የተያዙት ሰዎች አብዛኞቹ በእድሜ የገፉ ሲሆኑ እስካሁን ባለው መረጃም እድሜያቸው በ49 እና 56 ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው በህጻናት ላይ መተያቱ የተለመደ አይደለም ተብሏል።

የሰላሳ ሰዓት እድሜ ካለው ከዚህ ህጻን ውጪ እስካሁን በበሽታው የተያዙ እድሜያቸው ትንሽ ከሆኑ ህጻናት መካከል ሴንጋፖር ውስጥ የተገኘው የስድስት ወር ህጻንና አሁን አውስትራሊያ የሚገኘው ዉሃን ውስጥ እንደተያዘ የተነገረለት የስምንት ዓመት ታዳጊ ነው።

Report Page