#BBC

#BBC


በኦሮሚያ ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ ታጣቂዎች መኃል አንዱና የቀድሞ የኦነግ ሰራዊት የጦር መሪ ነበር ተብሎ የሚታመነው አቶ ኩምሳ ድሪባ (በትግል ስሙ መሮ) ከሰሞኑን የሱ ክንፍ በስፋት ይንቀሳቀስበታል በሚባለው ኦሮሚያ ምዕራባዊ ክፍል አለ ስለሚባለው የጦር እንቅስቃሴ ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር። 

BBC : አሁን አካባቢው ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?

ጃል መሮ : የአሁኑን በጥቂቱ ለየት የሚያደርገው የስልክ እና የሞባይል ዳታ ግንኙነት መቅረጡ ነው። ህብረተሰቡ እየተገናኘ አይደለም። እንዳሰቡት በኦሮሞ ነፃነት ጦር ላይ የበላይነትን ማሳካት ስላልቻሉ በተለየ መንገድ ሊሄዱበት የወሠኑት ውሳኔ ነው እየተከናወነ ያለው። ከፍተኛ ጦር በበርካታ ተሽከርካሪዎች እየመጣ ነው የቆየው። ከዚህ በተጨማሪ ባለፈው ጊዜ በአስቸኳይ ለአጭር ጊዜ ያሰለጠኗቸው ኃይሎች ወደዚህ መጥተዋል። ይህ ሚስጥር አይደለም። በህብረተሰቡ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ይታያል። በህዝቡ ተሽከርካሪዎች ነው የሚገለገሉት እንዘደዚሁ ይመጣሉ መመለስ የለም። 

BBC : አይመለሱም ስትል ተመተው እዚህ ይቀራሉ ማለት ነው? ብታብራራልን።

ጃል መሮ : አጭር መልስ እኮ ነው!

BBC: በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 17 ተማሪዎች በታጠቀ ኃይል መታገታቸድ ይሰማል። በደምቢ ዶሎና ጋምቤላ መኃል የእናተ ጦር ነው ያገታቸው ይባላል።

ጃል መሮ: ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማሁ ያለሁት ካንተ ነው። የኛ ጦር እንደዚህ ያለ ተግባር አይፈፅምም። ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር የሚያይዘን ነገር የለም። ይህ ፍፁም አይሆንም፣ ከዚህ በፊትም ሆኖ አያውቅም፣ ወደፊትም አይደረግም። 

BBC : እነ ጃል መሮ ከህወሓት ሰዎች ጋር አብረው እየሰሩ ነው ብለው የሚያነሱ አሉ፤ ሰሞኑን መቐለ ነበርክ ተብሎም ይወራል።

ጃል መሮ : ስትፈልጉ መሮ ሞቷል፣ ስትፈልጉ መቐለ ነው ያለው፤ የኦሮሞ ልጆች የሚፈልጉት ነገር አለ። ኦሮሞ ራሱን ችሎ፤ የራሱን ፖለቲካ፣ የራሱን የጥበቃ ኃይል አስተዳደር እና ፖሊስ ኖሮት የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ መመለስ ይችላል ብሎ ከማሰብ ይልቅ በተጋሩዎች በኩል ነው፤ በአማራዎች በኩል ነው የሚያዋጣን ብለው ሰበብ ይፈልጋሉ። መሮ ወይም የኦሮሞ ነፃነት ጦር ከነዚህ ጋር ይሰራሉ ሊሉ ይሻሉ እኛ ራሳችንን ችለን ነው የምንቀሳቀሰው። ለማንኛውም እኔ የምናገኘው በኦሮሚያ ጫካ ውስጥ በወለጋ ቡና ስር ነው። 

BBC : በወለጋ ኢንተርኔት እና ስልክ ተቋርጧል በሚባልበት ጊዜ አንተን ማግኘት እንዴት ተቻለ?

ጃል መሮ : እውነት ነው ከመላው ኦሮሚያ መገናኛ ዘዴ ቢቋረጥ፣ ከመላው ኢትዮጵያም ቢቋረጥ አቅም እንዳለው የኦሮሚያ ነፃነት ጦር የራሱ የሆነ ኔትዎርክ እንዳለው ከዚህ ነው የምትረዳው። ጦሩ እየተገናኘ ነው ያለው። 

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

Report Page