#BBC

#BBC


BBC : ከምርጫው በኃላ ረብሻና ብጥብጥ ይነሳል ብለህ ትሰጋለህ? ያ እንዳይሆን ከወዲሁ ምን ሊደረግ ይገባል?

JAWAR : የመንግስት አካላት ከአላስፈላጊ ጣልቃገብነት፣ ለገዢው ፓርቲ አለማዳላት፣ ግጭቶችን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ነገሮችን አለማድረግ ኃላፊነት አለባቸው ይሄን ኃላፊነት መወጣት አለባቸው። የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ከፍተኛ የሆነ ኃላፊነት አለባቸው ምክንያቱም ይህ ምርጫ ህዝባችን ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ፤ ምናልባት ለሁለተኛ ጊዜ ሊሆን ይችላል ከ97 ምርጫ ወዲህ የሚፈልገውን ፓርቲ፣ የሚፈልገውን መሪ፣ የሚፈልገውን እጩ የሚመርጥበት ስለሆነ ተቃዋሚዎችም ለግጭት በማይጋብዝ መልኩ፣ በተረጋጋ መልኩ ህዝቡን ሲቀሰቅሱ፣ ሲያደራጁ ለዘብ ባለ መልኩ መሄድ ይጠበቅባቸዋል። ይሄን ለማድረግ መተማመን ይጠይቃል። ይሄን መገንባት ላይ ከሰራን ለ50 እና 60 ዓመታት ብዙ ወጣቶች የተዋደቁለት ፍትሃዊ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችለንን ጅማሮ ላይ እንደርሳለን። ያ ካልሆነና ግን ገዢው ፓርቲ እንደለመደው 27 ዓመት ሲያደርግ እንደነበረው ወደማፈን የሚሄድ ከሆነ የተቃዋሚው ኃይልም በቁጭት እና በንዴት እየተመራ የሚሄድ ከሆነ ከምርጫ በኃላ ከፍተኛ አደጋ ሊመጣ ይችላል። ደጋግሜ እንደምለው ይሄ ምርጫ በአግባቡ ከተጠቀምንበት የሀገራችን ትንሳኤ ሊሆን ይችላል። ያለአግባቡ የምንሄድበት ከሆነ ግን ወደ ሃገር መውደቅ፣ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ሊወስደን ይችላል።

BBC አንተ እንደ ግለሰብ አለመራምረጋጋት ሊኖር ይችላል ከምርጫው በኃላ የሚል ስጋት አለህ?

JAWAR : አዎን! ምክንያቱም እኔ የፖለቲካ ተመራማሪ ነኝ። ብዙ ለውጦችን አጥንቻለሁ፤ ብዙ ሽግግሮችን በአካል ሄጄ የተሳኩትንም የተጨናገፉትንም አይቻቸዋለሁ። ሲከናወኑም ከተከናወኑም በኃላም። በአረብ ሃገራት፣ ኤዥያ፣ ምስራቅ አውሮፓ፣ ደቡብ አሜሪካ፣ እንደ observer እንደ academic በቅርብ ሳያቸው ስለነበረ ስህተቶች እንዴት ችግር ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ስለምገነዘብ ስጋቶች አሉኝ፤ ፍርሃቶች አሉኝ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን እንደያዙ በማግስቱ ማድረግ የነበረባቸው ከተቃዋሚው ጋር ቁጭ ብለው የሰፋውን የፖለቲካ ምህዳር እንዴት በአግባቡ እንጠቀምበት? በምርጫ ቀነ ገደብ ላይ፣ በምርጫ አካሄድ ላይ፣ በምርጫ አማራሮች ላይ፣ ህግጋቶች ላይ ጠለቅ ውይይትና ስምምነት ያስፈልጋል ስል ነበር። ያ ባለመሰራቱ በቂ ዝግጅት ስላልተካሄደ፣ በቂ የማስተማመኛ ስራዎች ስላልተሰሩ ስጋት አለኝ። ትልቅ ስጋት አለኝ። የተስፋ ጭላንጭሎችም ይታዩኛል!

Report Page