Bbb

Bbb


site logo
site logo

የትግራይ ተወላጆች ያለፍርድ በአስከፊ እስር ቤቶች ታጉረው እንደሚገኙ ተገለጸ


“በሺሕዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች፣ ያለፍርድ በጊዜያዊ እስር ቤቶች ተይዘው ይገኛሉ፤” ሲል ሮይተርስ ዛሬ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል።

እንደ ሪፖርቱ ጥቆማ፣ በአሁኑ ወቅት 9‚000 የሚኾኑ ተወላጆች በእስር ቤቶቹ ሲገኙ፣ ቢያንስ 17 እስረኞች ለኅልፈት ተዳርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የሚካሔደው ጦርነት 19 ወራትን በአስቆጠረበት ኹኔታ፣ 3‚000 የሚኾኑ እስረኞች፣ በሚዛን ተፈሪ ከተማ በሚገኙና በእጅጉ በቆሸሹ 18 የእስር ቤት ክፍሎች ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ፤ ብሏል የሮይተርስ ዘገባ።

በተመድ እንደተገመተው፣ መንግሥት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ከኅዳር እስከ የካቲት ባሉት ወራት፣15,000 የሚኾኑ የትግራይ ተወላጆች ተይዘዋል።

ሮይተርስ በበኩሉ፣ ከ17 የቀድሞ እስረኞች እና በሳተላይት ፎቶ ተደግፎ ባደረገው ማጣራት፣ ያለፍርድ ተይዘዋል ያላቸው እስረኞች ብዛት፣ ተመድ ከሚገምተው ቢያንስ በ3‚000 እንደሚበልጥ ተመልክቷል።

የሮይተርስ ልዩ ዘገባ እንደሚለው መንግሥት አብዛኞቹ እስረኞች ተለቀዋል ቢልም 9000 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች አሁንም ታስረው የገኛሉ።

አብዛኞቹ የእስር ቦታዎች ለሌላ ተግባር የተሠሩ፣ ጠባብና የቆሸሹ ናቸው ሲል ዘግቧል ሮይተርስ። ሪፖርቱ በመቀጠል የእስረኞቹ አያያዝም ዓለም አቀፍ ሥርዓትን ያልተከተለ ነው ብሏል።

የትግራይ ተወላጆች በሃገሪቱ ከሚገኙ 120 ሚሊዮን ከሚሆኑ ሕዝቦች ስድስት በመቶውን ብቻ ሲይዙ ለሦስት ዐስርት ዓመታት ህወሓት የመንግሥትን ስልጣን በተቆጣተጠረበት ወቅት በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን ካለፍርድ አስሮ ነበር ሲል ሪፖርቱ አስታውሷል።

የህወሓት ኃይሎች ባለፈው ኅዳር ወደ መዲናዋ እየተጠጉ ባለበት ሰዓት ጠ/ሚ ዓብይ አህመድ አስቸዃይ ግዜ አዋጅ በማወጅ ካለፍርድ ሂደት ተጠርጣሪዎች የሚያዙበትን ሁኔታ ፈጥረዋል። አዋጁም እስከ የካቲት አጋማሽ ድረስ ቆይቶ ነበር ካለ በኋላ ሪፖርቱ ሲቀጥል የተመድ የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሸሌት “አብዛብኞቹ ታሳሪዎች ተራ የትግራይ ተወላጆች ናቸው” ሲሉ የኢትዮጵያው ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ደግሞ “ሰዎች በማንነታቸው ምክንያት መያዛቸው አሳስቦኛል” ማለቱን አስታውሷል።

ሦስት የአፋር ክልል ነዋሪዎች 12,000 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች መታፈሳቸውን እንደነገሩት ሮየተርስ ጠቅሶ ተክክለኛ ቁጥሩን ግን ማረጋጋአጥ አልቻልኩም ብሏል።

ፖሊስና የኢትዮጵያ መንግስት ግን ኢላማ ያደርግነው ተጠርጣሪ የህውሓት ደጋፊዎች ላይ ነው ይላሉ።

ወባ በተንሰራፋበትና ቆሻሻ በበዛበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ታስረው እንደነበር አንዳንዶች ለሮይተርስ ተናግረዋል። እጅግ በተጨናነቀ ሁኔታ ስለነበሩም በጀርባቸው መተኛት እንደማይችሉና የውሃ እጥረት እንደነበር እንዲሁም በቀን አንድ ግዜ ለ15 ደቂቃ ብቻ የመጸዳጃ እረፍት እንደሚሰጣቸው በሚዛን ተፈሪ ተይዘው የነበሩ እስረኞች ተናግረዋል።

5 ሜትር በ6 ሜትር በሆነ ጠባብ ክፍል ውስጥ እስከ 183 ሰዎች ታጉረን ነበር ሲል አንድ እስረኛ ለሮይተርስ ሲናገር ሌላኛው ደግም እርሱ ተይዞ በነበረበት ክፍል ውስጥ 176 ሰዎች ነበሩ ብሏል።

በሚዛን ተፈሪው እስር ቤት በጥበቃ ሥራ ላይ ተሰማርቶ እንደነበር የሚናገረው አንድ ግለሰብ እንዳለው እስር ቤቶቹ የተሰሩት ከ70-80 ሰዎችን ለመያዝ ነው።

የአውሮፓ የሰቆቃንና የኢሰብአዊ ድርጊቶች ተከላካይ ኮሚቴ አንድ እስረኛ ቢያንስ አራት ስኩየር ሜትር ቦታ ማግኘት እንዳለበት ይደነግጋል። በሚዛን ተፈሪ የሚገኙት እስር ቤቶች ግን በ 4 ስኩየር ሜትር ውስጥ ከ20 በላይ እስረኞች ተይዘውበታል። ጌትነት የተባሉ የእስር ቤቱ ተጠባባቂ ሃላፊ እንደሚሉት ቦታው 2,900 እስረኞችን የያዘና ሁለት ለቢሮ የሚያገለግሉ ክፍሎችን በሳንባና ሄፒታይተስ የተጠቁ ሰዎችን አሳርፈንበታል ብለዋል። እስረኞች በቅማልና ሌሎች ነፍሳትና ብሽታ ተሰቃይተናል ሲሉ አቶ ጌትነት ግን ባለስልጣናት ለእስረኞች የተመቻቸ ሁኔታ ለመፍጠር የታቻላቸውን አድርገዋል ብለዋል።

በህዳር 4 ተይዞ የነበረ አንድ የትግራይ ተወላጅ የመንግስት ሰራተኛ እንዳለው እስር ቤቶቹ በጣም የተጨናነቁና እግርና ጭንቅላት እያጋጠሙ እንደ ሳርዲን ታጭቀው እንደከረሙ ተናግረዋል።

ሮይተርስ በምርመራው ቢያንስ 4 እስረኞች በሚዛን ተፈሪ እስር ቤት ተይዘው በቆዩበት ወቅት በህመም መሞታቸውን መረዳት ችሏል። እስረኞች በሞቱ ቁጥር ማታ ማታ ለቅሶ እንሰንማ ነበር ሲል አንድ እስረኛ ተናግሯል።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨስቲ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ግዛው ወዳጆ በአካባቢው የወባ ወረርሽኝ እንዳለና እርሳቸው እስከሚያውቁት ድረስ መድሃኒት እንዳልተረጨና እስረኞችም አጎበር እንደሌላቸው ተናግረዋል። ብዙ እስረኞች መድሃኒት እንደማያገኙ ሲናገሩ ዶ/ር ግዛው በበኩላቸው የአካባቢው ባለሥልጣናትና የዓለም ቀይ መስቀል ማህበር ለአንዳንዶቹ እስረኞች የህክምና ውጪ መክፈል ችለው ነበር ብለዋል።

ሚዛን ተፈሪ ብቸኛው እስር ቤት አልነበረም የላል የሮይተርስ ልዩ ዘገባ። ከመዲናዋ 220 ኪሜ በሚርቀውና ሾኔ በምትባል ከተማ የሚገኘው የወጫሞ ዩኒቨርሲቲ አንድ ግቢ ውስጥ 1200 የትግራይ ተወላጆች ለ 8 ወር አካባቢ ተይዘው ነበር። የወረዳው ቃል አቀባይ አለማየሁ ባከራ እንደሚሉት እስረኖች ሳይሆኑ በመጠለያነት የሚቆዩበት ነው ብለዋል። ባለፈው አመት ከሳውዲ የተመለሱ ናቸው ሲሉ አክለዋል።

በኢትዮጵያ ባሉ የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው የነበሩ አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች የህወሓት ኃይሎች ወደ ትግራይ ካፈገፈጉ በኋላ ባለፈው ጥርና የካቲት ተለቀዋል። በመጋቢትና በሚያዚያ የተለቀቁም ነበሩ። አሁንም ግን በሺሕዎች የሚቆጠሩ በአፋር ታስረው ይገኛሉ።


Report Page