audit
የኦዲት ስራ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የ2012 ዓ.ም በጀት ሂሳቡን በውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በዚህ ውድድር ለመሳተፍ በአንድ አቃፊ የሚያስከፍሉትን ገንዘብና ምርመራውን በማጠናቀቅና ሪፖርቱን የሚያቀርቡበትን ጊዜ በመግለጽ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በታሸገ ኤንቨሎፕ እንግሊዝ ኤምባሲ ወደ ምስራቅ አጠቃላይ ቴክኒክና ሙያ በሚወስደው መንገድ ይመናሹ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው ጽ/ቤታችን በገጽ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በውድድሩ የሚቀርቡ የኦዲት ድርጅቶች የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የቫት ምዝገባ ሠርተፍኬት ኮፒ እና ደብል ኢንትሪ ፒስትሪ ሲስተም የሚችል ሆኖ ደረጃውን የሚገልጽ መረጃዎችን ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር መያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አግር ኳስ ክለብ
________________
Posted:አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2012
Deadline:July 24, 2020
________________