audit የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት
Walia Tenderለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 0050/ የአገልግሎት ግዥ /2012 ዓ. ም
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የደቡብ ምርጥ ዘር ከ2011ዓ/ም-2012 ዓ/ም ድረስ ያለ የሁለት አመት የድርጅቱን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቶች በኢትዮጵያ የሂሳብና ኦዲተሮች የምዝገባ ፍቃድ የተሰጣቸው እና ለ2012ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የሙያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማያያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች አጠቃላይ የስራ ልምዳቸውን በተለይ በማምረቻ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለኦዲት ስራ የሚመደቡቋሚ ባለሙያዎች ብዛት፣የትምህርት ደረጃ፣የስራ ልምድ ደረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለ አዲት ድርጅቱ አቋም የሚያስረዳ ፕሮፋይል ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች ድርጅቱ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የኦዲት ድርጅቱ ከ5ዓመት ያላነሰ የኦዲት አገልግሎት የሰጠ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ሲኖርባቸው ብዙ ልምድ ያላቸው የተሻለ ተመራጭ ይሆናል፡፡
- ኦዲት ስራውን ለመጀመር የሚወስድበትን የሪፖርት ጊዜ በስራ ቀናት በዝርዝር መግለፅ ይኖርበታል፡፡ ስራውን በአጭር ጊዜ የሚጨርሱ የተሻለ ተመራጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታው ሰነድ አቀራረብ በሁለት ፖስታ ሆኖ የቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ በጨረታው መክፈቻ ቀን የሚከፈት ሆኖ የቴክኒካል አፈፃፀማቸው ከ85% በላይ ያገኙ ተጫራቾች ለስራው ብቁ ናቸው ተብሎ ሲገመት የቴክኒካል አፈፃፀማቸው ከ85% በታች የሆኑ ተጫራቾች ከጨረታው ተሰርዘው የፋይናሻል ፕሮፖዛል እንደታሸገ ተመላሽ ይደረጋል፡፡ የቴክኒካል ፕሮፖዛላቸው ከ85% በላይ ያገኙ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ፋይናሻል ፕሮፖዛል/ ለመክፈት ጥሪ የተደርገላቸው ተጫራቾች በተገኙበት ሀዋሳ ላይ በድርጅቱ ፅ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ሲፒኦ 2% በደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ መቅረብ አለባቸው፡፡
- ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይችልም ቀርቦ ቢገኝ ተጫራቹ ጨረታውን ከመሳተፍ ይታገዳል፡፡
- ማናቸውም የመንግስት ታክስና ግብር ወጪ የሚሸፈነው በአገልግሎት ሰጪው በተጫራች ድርጅት ይሆናል፡፡
- የሂሳብ ምርመራው የሚካሄደው በድርጅቱ ጽ/ቤት ሀዋሳ ላይ ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ ግዥና/ፋ/ንብ/አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ/ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት ሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ከፍል ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ15 ኛው ቀን እስከ 8 ፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አካባቢ በወጣ በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ታሽጐ በእለቱ በ8 ፡30 ሰዓት በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 8 ተጫራቶች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡ ፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት አስቀድመው ሀዋሳ በድርጅቱ ጽ/ቤት ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በተገለፀ በ5 ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል መፈራረም አለበት፡፡ ካልፈረሙ ለጨረታው 2% ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በስልክ ቁጥር፡-046220 1752/2285/2117
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት
________________
Posted: አዲስ ዘመን ሐምሌ 21 ቀን 2012
Deadline: August 11, 2020
________________