#AA

#AA


በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማ አስገድዶ ከመድፈር ሙከራ ጋር ተያይዞ ህይወት አጥፍቷል የተባለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ጽኑ አስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

ዘገየ መስፍን እና ንጉሴ ተክለማሪያም በሚል በሁለት ስሞች የሚጠራው ይሄው ግለሰብ ድርጊቱን ፈጸሟል የተባለው ከአዲስ አበባ ለቤት ሰራተኝነት ቀጥሮ ባመጣት ሴት ላይ ነው።

የፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወይዘሮ ዘርትሁን ያዘው ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቡ ጥር 20/2011ዓ.ም. ሰራተኛዋ በቤቱ ውስጥ ሌሊት ተኝታ ባለችበት ሁኔታ በማፈን አስገድዶ ለመድፋር ይሞክራል። ሰራተኛዋም እራሷን ለመከላከል ብትሞክርም አንገቷን አንቆና አፍኖ በመደብደብ ባደረሰባት ከባድ ጉዳት ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።

ግድያውን ከፈጸመ በኋል በዚሁ ዕለት በአካባቢው ልዩ ስሙ ሾላ በር በሚባል ስፍራ አስከሬኑን ሜዳ ላይ ጥሏል በሚል በከባድ የሰው መግደል ወንጀል መከሰሱን ባለሙያዋ አስረድተዋል።

የግለሰቡም ድርጊት በአቃቢ ህግ ማስረጃዎች ተረጋግጦበት ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 28 ቀን 2011ዓ.ም. በዋለው ችሎት በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን አስታውቀዋል። ክሱን እንዲከለካል እድል ቢሰጠውም ባለመቻሉ ቅጣቱ በግለሰቡ ላይ መጽናቱንም አመልክተዋል፡፡

Via #ኢዜአ

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page