AA

AA


በዒድ ሰላት ወቅት የተከሰተው ክስተት በክርስቲያኑና በሙስሊሙም መካከል የተፈጠረ አይደለም።

አንዳንድ አካላት ችግሩን ከመንግስት ጋር ለመሰያያዝ መሞከራቸውም የተሳሰተ መሆኑን አረጋግጠናል።

በዒድ ሰላት ወቅት የተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ በስፍራው ከነበሩ በጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎቻችን ደርሶናል። በአንድ ፌደራል ፓሊስ ድንገት (ባርቆብኝ ነው ብሏል) በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ ምክንያት የተፈጠረ ግርግር ነበር።የአስለቃሽ ጭሱ እንደተተኪሰ በቦታው የነበሩ የበአሉ ታዳሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ተደናግጠዋል።ወደ ፎደራል ፓሊሱ በማቅናት ይዘውታል።ፓሊሱም ድንገት ባርቆበት እንደሆነ ተናግራል-ይህ በፀጥታው ሀይል መጣራት ይኖርበታል-ሆኖም ህዝቡ ከፍተኛ የሆነ መረበሽ ውስጥ ስለገባ ለመግባባት አልተቻለም።

------

በመጨረሻም የፌደራል ፓሊሱ በኤግዢቢሽን አካባቢ ወደ ሚገኘው የፎደራል ፓሊስ ካንፕ እዲገባ ተደርጎል።ይህን ተከትሎ ሌሎች ፓሊሶች ከካምፑ ሲወጡ ቶክሱ የፈጠረው ግርግር ባለመረጋጋቱ ችግሩ ሊባባስ ችሏል።

----

ከዚህ በተረፈ ከስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ እምነት ተለከታዮች ጋር ችግሩን የሚያያይዘው ነገር አለመኖሩ ተረጋግጣል።በመንግስት በኩልም ሆነ ተብሎ የተፈጠረ ችግር አለመኖሩን አረጋግጠናል።በመሆኑም ህዝቡ እንዲረጋ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

Report Page