Vi ins የአንዳቤት ወረዳ ገንዘብ ኢ
Walia Tenderግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጐንደር ዞን የአንዳቤት ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
- ሎት 1 የመኪና ጎማ
- ሎት 2 የመኪና መለዋለጫ እቃ እና
- ሎት 3 የበር እና መስኮት ወይም የጠቅላላ ብረታ ብረት ብየዳ ስራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፋ የተጋበዛችሁ በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ የመወዳደሪያ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ/ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማስያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 መግዛት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡00 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአንዳቤት ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ማሻሻያ ማድረግና ራሣቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡
- የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ/ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቢቱ ከጨረታው 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረቡ ሲሆን ሁሉም የእቃዎች ዋጋመሞላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን መግለጽ የድርጅቱ ማህተም መርገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር በ058547068 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአንዳቤት ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013
Deadline:በ16ኛው ቀን 3፡30
© walia tender