VI SL CMP FR VU TX BU PR በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ

VI SL CMP FR VU TX BU PR በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ

Walia Tender

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት በግሼ ወረዳ ውስጥ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ጥቅል ግዥ 

ሎት 1.የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣
ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ፣
ሎት 3 የኮምፒውተር ቀለምና የፎቶ ኮፒ ቀለም፣
ሎት 4.ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣
ሎት 5 ቋሚ የቢሮ እቃ፣
ሎት 6 አላቂ የጽዳት እቃ፣
ሎት 7 የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ፣
ሎት 8 የተዘጋጁ ልብሶችና ብትን ጨርቅ፣
ሎት 9 ጫማዎችና የቆዳ ውጤቶቸ 
ሎት 10.የስፖርት ማቴሪያል፣
ሎት 11 የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣
ሎት 12 የተለያዩ ህትመቶች

በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ 

  1. በዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ ንግድ ስራ ፍቃድ ያለው/ያላት፡፡ 
  2. 2የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላቸው፡፡ 
  3. ለተሽከርካሪ መለዋወጫ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡ 
  4. የግዥው መጠን ከብር 200.000/ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር -4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልፅ የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃ ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ :: 
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ሎት1 ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ለሎት 2 ብር 50/ሃምሳ ብር/ ሎት3 ብር 40/አርባ ብር/ሎት 4.ብር 50/ሃምሳ ብር/ ሎት 5 30/ሰላሳ ብር ሎት 6, 30/ሰላሳ ብር ሎት 7.ብር 50/ሃምሳ ብር/ሎት 8.ብር 40/አርባ ብር/ ሎት 9.ብር 30/ሰላሳ ብር/ ሎት 10.ብር 20/ሃያ ብር/ሎት1 ብር 50/ሃምሳ ብር/ ሎት 12.ብር 20/ሃያ ብር ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 መግዛትና ማግኘት ይችላሉ፡፡ 
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 ፐርሰንት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሆኖ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ከባንክ የተረጋገጠ Letter of credit ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የእለት ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ለየብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
  9. ተጫራቾች ለተጫረቱበት ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 1% ሲያሲዙ በየሎቱ ለየብቻው ማስያዝ አለባቸው:: 
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት በግዥ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና በመሙላት እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት አለበቸው:: 
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 06 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል ተጫራቶች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡ 
  12. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መግባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
  13. ጨረታው በሎት መሆኑ ይታወቅ :: 
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0338119866/0338990102 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 
  16. ከላይ ያልተገጸ ካለ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 
  17. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በአላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት 

__________________

Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 10፣2013

Deadline:በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00

__________________
© walia tender


Report Page