VI የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን

VI የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ 

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እና ጎማዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት አስፈልጓል፡፡ 

ተ/ቁ የዕቃው ዓይነት 
ሎት 1 የተለያየ የመኪና መለዋወጫ እና ጎማዎች ግዥ ጨረታ 


በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ:: 

  1. . ከዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለጸ መሆን አለበት፡፡ 
  2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ:: 
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው:: 
  4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለ ስልጣን የዘመኑ ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው:: 
  5. አማራጭ ዋጋ ከዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም:: 
  6. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ 50,000.00 ብር(ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  7. እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 60ቀንና ከዚያም በላይ በመሆን ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል/ ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡ 
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን በትክክል መጻፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም::
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው::
  11. .ተጫራቾች ፒያሳ አ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከፍ ብሎ በሚገኘው ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ዋናው መ/ቤት 1ኛ ፎቅ የግዥና ፋይናንስ ቢሮቀርበው ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ:: 
  12. ጨረታው በ26/01/2013 ዓ.ም ከረፋዱ 6:00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8:00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን በመ/ቤቱመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል 
  13.  ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፣ 
  14. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: 
  15. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

 መረጃ:-በስልክ ቁጥር 01-11-26-5665 /0111265199 መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

ፌዲራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን 

__________________

Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 8፣2013

Deadline:26/01/2013

__________________
© walia tender


Report Page