Used aa rev airport5

Used aa rev airport5

Walia Tender

የልዩ ልዩ ንብረቶች የግልጽ ጨረታ ቁጥር 01/2012 እና የሐራጅ ጨረታ 01/2012 የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ

ኤሌክትሮኒክስ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ሞባይሎች፣
ላፕቶፖች፣ ሞተር ሳይክሎች፣ አሳይክሎች፣
የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ቁጥር 01/2012 በ09/10/2012 ዓ.ም እና ሐራጅ ጨረታ ቁጥር 01/2012 በ11/10/2012 ዓ.ም የምናካሂድ በመሆኑ የቀጣይ 2012 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ለሁሉም ተደራሽነት ባለው መልኩ በጋዜጣ ማስታወቂያው እንዲነገርልን እንጠይቃለን፡፡
በመሆኑም:

በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬትና የቫት እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት የቫት ሪፖርት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ /ክሊራንስ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቶች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-7፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ::
በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና( CPO) በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን እስከ 09/10/2012 ዓ/ም 3፡ 00 ሰዓት በመገኘት መመልከት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው ሰኔ 09/2012 ዓ. ም ከጠዋቱ፡ በ4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4:30 ሰዓት የሚከፍት ይሆናል፡፡
በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡ ትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበት ቅጾች መሠረት ለተመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፣ የተጫራቾች ስም፣ አድራሻ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) እና ከላይ በተቁ የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወገገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።
ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
አሸናፊ ተጫራቾች ማሽነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ ያሽነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታው አሸናፊ ተጫራቶች ያሸንፉበትን ዋጋ ክፍያ ከፈጸሙ በ5 ቀናት ውስጥ ንብረቱን መረክብ ይኖርባቸዋል፡፡
ከላይ በተ/ቁ8 እና በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰነደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) እና ለንብረት የከፈሉት ዋጋ ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
በተራ ቁጥር 1-0 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም ሐራጅ ጨረ ታ ሰኔ 11/10/2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሄድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ገርጂ እና ካርጎ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር/ ለየዘርፉ በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርበታል፣
. ቅ/ጽ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ቦሌ ኤርፖርት 0118678216 እና 0116628868

የተቋሙን ዌብሳይት www.erca.gov.et ይመልከቱ፡፡ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ ጽ/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 30 ቀን 2012

Deadline: July 19, 2020


© walia tender

Report Page