Usd haf car አንበሳ ኢንሹራን

Usd haf car አንበሳ ኢንሹራን

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን

የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና የኩባንያው ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን/ የተለወጡ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. የመኪኖቹን/የንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ (ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል) በስራ ሰዓት በመገኘት ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ማየት ይችላሉ፡፡
  2. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውንና የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው አዲሱ የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና መ/ቤት ካሣ መምሪያ አንደኛ ፎቅ ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የያንዳንዱን ተሽከርካሪ/ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 06 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ካሣ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ/ንብረት የመነሻ ዋጋ ብር 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች በማስያባርነት ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ጥቅምት 07 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ በኩባንያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወይም ንብረት ሙሉ ክፍያ በ 5 ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ በ10 ቀናት ንብረቶቹን ካላነሱ ለሀያ ቀና በየቀኑ ብር 30.00 / ሰላሳ ብር/ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከፍለው ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡
  7. ለጨረታ ከቀረቡት ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ዓይነት የስም ማዛወሪያ፣ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፡፡
  8. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116-352283 ወይም 0116-187000/6632947 በመደወል ወይም በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር መጠየቅ ይቻላል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው::
  11. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
  12. ጨረታውን በተመለከተ ለሚቀርብ ማንኛውም ማመልከቻ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  13. ተጫራቾች ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወደ ስማቸው ለማዞር ከተሸጠበትን ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ ወደ ሳማቸው ማዞር ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ግን ኩባንያው በተሽከርካሪው ላይ ለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር እና ለሚደርሰው ጉዳት ኩባንያ ኃላፊነት እንደማይወስድ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ

የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባልተገኙበት ጨረታውን እንዲከፈት እናሳስባለን፡፡

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)


Posted:ሪፖርተር መስከረም 24፣2013

Deadline:ጥቅምት 07 ቀን 2013


© walia tender

Report Page