Usd የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ

Usd የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ያገለገለ

  • የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣
  • የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣
  • ጀነሬተሮች፣
  • ንቃይ የአሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣
  • የእንጨት ኬጂ እና ካውንተሮች፣
  • የእንጨት የብረት እና የአሉሚኒየም በሮች ፣
  • አሮጌ ጎማዎች፣
  • የመኪና ባትሪዎች ፣ከጋራዥ ተመላሽ የመኪና መለዋወጫዎች እና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታውሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 6 ቀን ድረስ ቦሌ መንገድ ጌት ሃውስ ህንፃ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ ላገለገሉ ለቢሮ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 100 (አንድ መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ደምበል ሲቲ ሴንተር አንደር ግራውንድ በሚገኘው BMS 01B ቢሮ ቁጥር ወይም የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ፤
  2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ጦር ሃይሎች ከሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ጀርባ ጋና ኤንባሲ ከመድረሶ በፊት በስተ ቀኝ በሚያስገባው ኮብል ስቶን መንገድ ከኦሜጋ ት/ቤት 100 ሜትር ተሸግሮ በሚገኘው የባንኩ ግምጃ ቤት ፣ ብሄራዊ ቴያትር አከባቢ ከአዋሽ ባንክ ዋና መ/ቤት ጀርባ በሚገኘው የባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ እና ቦሌ ሩዋንዳ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም ጥቅምት 4 እና 6 ቀን 2013 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ሰዓት እከከ 10፡00 ሠዓት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  3. ገርዎች የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ቦሌ መንገድ ደምሰል ህንጻ BMS 01B ቢሮ ቁጥር ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ሰአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ።
  4. የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ዉን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% በተጨማሪነት መኖር አለመኖሩን በግልፅ በሰነዱ ላይ በፅሁፍ መግለፅ ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
  7. ጨረታው አርብ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በ10፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ስኞ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ስዓት ደምበል ሲቲ ሴንተር በ6ኛው አሳንሰር 4ኛ ፎቅ ግዥ እና ፋሲሊቲ አስተዳደር ቢሮ ፤ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተጫራቾች ባልተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
  8. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ (አማ)

ስልክ ቁጥር 0115576174

ፖሣ.ቁ 16936


Posted:ሪፖርተር መስከረም 24፣2013

Deadline:ጥቅምት 6 ቀን 2013


© walia tender

Report Page