Usd አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

Usd አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

Walia Tender

ግልጽ ዕቃ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2013

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም

የተሰባበሩ ወንበሮች ፣
የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
የተለያዩ ብዛት ያላቸው አሮጌ ወረቀቶችን

በጥቅል ዋጋ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቶች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ማንኛውም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. ተጫራቾች ሠነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያና ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ብር 5,000/አምስት ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቶች ዕቃዎቹን (ንብረቶች) በት/ቤቱ ግቢ ውስጥ በመገኘት መመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ ሃምሳ ብር /በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን በቢሮ 4 ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት 11ኛ [በአስራ አንደኛው / የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ 4 ይከፈታል።
  8. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ ተሞልቶና ኦርጅናሉ ኮፒው ተለይቶ በፖስታው ላይ ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች በጨረታ የሚያሸንፏቸውን እቃዎች ያሸነፉበትን ጥቅል ዋጋ ለት/ቤቱ ገቢ በማድረግ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ አንስቶ ባሉት5( አምስት ) የስራ ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን በራሳቸው ትራንስፖርት ከት/ቤቱ ግቢ ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች በጨረታ የሚሸንፏቸውን እቃዎች በተጠቀሰው ጊዜ የማያነሱ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ለመ/ቤቱ ገቢ የሚሆን መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን።
  11. መ/ቤቱ ለሽያጩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አምስት ኪሎ ቅድስት ማሪያም ሸዋ ዳቦ ፊት ለፊት አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን

በአራዳ ክ/ከተማ አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 11፣2013

Deadline:በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00


© walia tender


Report Page