USD DIRE REV 4

USD DIRE REV 4

Walia Tender

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት 

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ 

የግልጽ ጨረታ ቁጥር 0012/2013 

በጉምሩክ ኮሚሸን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ

  • ስፔርፓርት፣
  • አልባሳት ቁሳቁስ፣
  • ኢሌክትሮኒከስ፤
  • ኮስሞቲክስ፣
  • ቆርቆሮ
  • ጎማዎች፣
  • የቤት ክዳን ቆርቆሮ

ከመስከረም 16 ቀን 2013 ዓ ም ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም ለጨረታ በቀረበው ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴውን ያሳውቁበትን የቅርብ ጊዜ የተሰጠውን የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል። 

  1. ተጫራቶች እቃዎቹ በሚገኙበት በድሬዳዋ እና በሀረር መጋዘን ተገኝተው ማየት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም:: 
  2. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ዝርዝር ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሪሲት በመውሰድ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰአት እስከ 6 ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። 
  3. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ግቢ ነው:: 
  4. ተጫራች ለሚጫረተው ለእያንዳንዱ እቃዎች በሰጡት ዋጋ 5% በጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ከባንክ የተረጋገጠ (CPO) ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል። 
  5. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እስከ መስከረም 16ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 3፡45 ድረስ በድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ ተጫራች ተቀባይነት የለውም:: 
  6. ተጫራች ዋጋ ሲሰጥ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት። 
  7. ጨረታው በእለቱ መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ይከፈታል። 
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ላይ ባይገኙም ጨረታ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል። 
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል:: 
  10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል። 
  11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከብ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል። 
  12.  ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: 
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 025-1-12-49-28 መደወል ይቻላል። 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድ/ደ/ቅ/ጽ/ቤት 

__________________

Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 8፣2013

Deadline:መስከረም 16 ቀን 2013

__________________
© walia tender


Report Page