USD የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

USD የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2020/21

የተለያዩ አዲስ እና ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ያገለገሉ

የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣
አዲስ እና ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ፣
ጎማዎች እና ባትሪዎች ፣
የተለያዩ ዓይነት ብረታ የብረቶች ፣
የስቴሽነሪ ዕቃዎች እና
የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎችን

በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

  1.  ንብረቶቹን ከመስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም.ድረስ ቃሊቲ መንገድ ትራንስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከል ጎን በሚገኘው የቀድሞ አማልጋሜትድ ግቢ ውስጥ እናቃሊቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ 300 ሜትር ገባ ብሎ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ ብርሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ በስራ ሰዓት ብቻ በመገኘት ማየት ይችላሉ::
  2.  ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሠነድ ቄራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሠፈር ቅርንጫፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከመስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ተኩል (3፡30) ድረስ መውሰድ ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የዕቃ ዓይነት የጨረታ የመነሻ ዋጋቸውን 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (Commercial Bank of Ethiopia) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  4. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ አሸናፊ ለሆኑት ለሚገዙት ዕቃ ክፍያ የሚታሰብ ሲሆን ተሸናፊ ለሆኑት ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::
  5.  የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥኖች ማክሰኞ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሁሉም በአንድ ላይ ይዘጋሉ::
  6. ተጫራቾች ያስገቡት የጨረታ ሰነድ ማክሰኞ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ በሚገኘው የጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሠራተኞች የመዝናኛ ክበብ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል::

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

__________________

Posted:ሪፖርተር መስከረም 10፣2013

Deadline: ጥቅምት 10 ቀን 2013

__________________
© walia tender


Report Page