USD ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኃ

USD ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኃ

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኃ/የተ/የግ/ማሸገር ዳቦ ማምረቻ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን ማለትም ፉሩሽካ፣ ፉሩሽኬሎ፣ እንቅጥቃጭ፣ ገለባ (አነስተኛ መጠን እህል ያለው)፣ ንፁህ ገለባ፣አፈሪቻ(አቧራ)፣ ፊልትሮ ዱቄት፣ የተሰባበረ ዳቦ እና ሊጥ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ

  1. የዘመኑ ግብር የከፈላችሁ እና የንግድ ፈቃድ ያሳደሳችሁ እና
  2. ቫት ተመዝጋቢዎች የሆናችሁ ድርጅቶች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ እየጋበዘ፤ ለእያንዳንዱን ተረፈ ምርት በተናጥል የምትገዙበትን የጨረታው ዋጋ ማቅረቢያ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሳይደርስ በሚገኘው ፋብሪካችን በአካል በመቅረብ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

ጨረታው የጨረታ ማስገቢያ ካበቃበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ሆኖም የተጫራቾች መክፈቻ ዕለትና ሰዓት አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግድም::

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 10000.00 (አስር ሺህ) በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118279307 ወይም 0118279304 ወይም0118279284 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኃ/የተ/የግ/ማ

ሸገር ዳቦ ማምረቻ

__________________

Posted:ሪፖርተር መስከረም 10፣2013

Deadline:አልተገለፀም

__________________
© walia tender


Report Page