UNSC

UNSC

BBC

በትላንትናው የፀጥታው ምክር ቤት ሰብሰባ ላይ ሀገራት ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

በምክር ቤቱ ኢትዮጵያን የወከሉት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ መንግሥታቸው ባለፈው አንድ ዓመት ከህወሓት የተቃጣበትን ወታደራዊ አደጋ መመከቱን ተናግረዋል።

መንግሥት ምግብን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቅሳቁሶችን በትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ለሚፈልጉ ሰዎች ከተባበሩት መንግሥታት ጋር በመተባበር ሲያቀርብ እንደነበር ተናግረዋል።

አምባሳደር ታዬ ለመልሶ ግንባታ ብሎም ለተለያዩ ድጋፎች መንግሥት እስካሁን መቶ ቢሊዮን ብር ያህል ማውጣቱን እንዲሁም ለሰብአዊ ድጋፍ እንዲያመች በሚል የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉን ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

"ይህ ሁሉ ከንቱ ሆኖ ቀርቷል" ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል። "በዚህ የወንጀል ቡድን ምክንያት የትግራይ ሕዝብ ያስፈልገው የነበረውን አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እያገኘ አይደለም" ሲሉ አምባሳደር ታዬ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

አምባሳደር ታዬ ፥ በአማራ እና በአፋር ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎችም በየበራቸው ላይ ተገድለዋል ሲሉም አምባሳደር ታዬ ገልጸዋል።

"መንግሥት ወደ ትግራይ ምግብ እና መድኃኒት ጭኖ የላካቸው ተሽከርካሪዎች የጦር መሳሪያዎችን እና ወጣት ተዋጊዎችን እያጓጓዙ ነው። ወጣቶቹ ከወንድሞቻቸው ጋር አንድም የሕዝብ ጥቅም በሌለበት ለጥቂት ስግብግብ ሰዎች ሲባል እንዲዋጉ ተገደዋል" ብለዋል አምባሳደሩ።

አምባሳደሩ "ለፖለቲካዊ ውይይት የሚደረጉ ጥሪዎችን እናከብራለን" ብለዋል።

የምዕራባዊያኑ መገናኛ ብዙኃን ብሎም የአንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሠራተኞች እንዲሁም አመራሮች ለህወሓት በይፋ ድጋፋቸውን ሰጥዋል የሚል ክስም አሰምተዋል።

አምባሳደሩ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅሟል የሚል ሐሰተኛ ሪፖርቶችን ሲወጡ ነበር ብለዋል።

አምባሳደር ታዬ የህወሓት ደጋፊዎች ለቡድኑ የመገናኛ መሳሪያዎችን፣ የሳተላይት መረጃዎችን፣ መሳሪያዎችን እንዲሁም ተዋጊዎችን ከማቅረብ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ ችግር ለማገገም ዓለም አቀፍ ድጋፍን እንደምትፈልግም አምባሳደሩ ተናግረዋል።

አገራቸው የአፍሪካ ሕብረት የምሥራቅ አፍሪካ ወኪል ለብሔራዊ ውይይት ያቀረቡትን ሃሳብ ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን በተደጋጋሚ ማሳወቋን ጠቅሰዋል።

አህጉራዊ መፍትሄዎች ኢትዮጵያን ለመደገፍ ተመራጭ ናቸው ያሉት ታዬ ወደ ውይይት እንዲሁም ወደ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለማምጣት የሚደረገው መንገድ ቀጥ ያለ ወይም ቀላል እንደማይሆንም ተናግረዋል።

"በዚህም ምክንያት መንግሥት በአሁን ሰዓት ይህንን የወንጀል ቡድን የማስቆም ሥራ መስራት ላይ ነው ትኩረቱ" ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል።


#ቻይና

ቻይናን የወከሉት ዣንግ ጁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው ሁኔታ የፖለቲካ፣ የታሪክ፣ የብሔርና ሌሎች ምክንያቶች ጥምር ውጤት መሆኑን ጠቁመው መፍትሔ የሚገኘው በአገር ውስጥ ብቻ መሆኑን አስምረውበታል።

በአህጉሪቱ ያሉ አገራትና ድርጅቶች ፖለቲካዊ እልባት ለማምጣት ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉም የአገራቸውን አቋም አስረድተዋል።

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አፍሪካዊ መፍትሄዎች ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት በድጋሚ ድጋፋቸውን ገልጸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ላሳዩትን በጎ ተግባር አመስግነው፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተለይም የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ሕብረት ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊውን ጊዜና ቦታ በመስጠት ድጋፍ መለገስ አለበት ብለዋል።

በተለይ አሜሪካና የተለያዩ አገራት የሚያደርጉትን ማዕቀብ በተመለከተም አስተያየታቸውን የሰጡት ተወካዩ፣ በንግድ ላይ ገደብ ማድረግ እና እርዳታን ማቋረጥ በፖለቲካው መፍትሄ ላይ ጣልቃ መግባት እንደሆነም አስረድተዋል።

ለፀጥታው ምክር ቤት አባላትም ምክራቸውን ያስተላለፉት የቻይናው ተወካይ አባል አገራቱ የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አመራር በማክበር ኢትዮጵያ የሰብአዊ አቅሟን እንድታሻሽል እና የሚሰጠው እርዳታም ሊጨምር ይገባል ብሏል።

በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ መወጣት፣ የውጭ ዜጎችን ጨምሮ የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ፣ ሰብአዊ እርዳታን ማመቻቸት እና ሰብአዊ ሁኔታው የከፋ እንዳይሆን ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።


#ዩናይትድ_ኪንግደም (UK)

ዩናይትድ ኪንግደምን ወክለው የቀረቡት ጄምስ ካሪዩኪ በቅርቡ በመንግሥት የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን እንደ ሰበብ በመጠቀም የሰብዓዊ መብቶችን እና ዓለም አቀፍ ሕጎች ችላ መባል እንደሌለባቸውም አስጠንቅቀዋል።

በተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ይፋ ባደረገው ሪፖርት ላይ ጾታዊ ጥቃት እንደ ጦር መሳሪያ መዋሉ፣ እንግልት እና ስቃይ፣ የሰላማዊ ዜጎች ጥቃት እና መፈናቀልን ጨምሮ በርካታ ጥሰቶችን በዝርዝር ጠቅሰው የሰብዓዊ መብት ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት የምርመራ ሪፖርት ውስጥ የተካተቱትን ምክሮች ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ሁሉም ወገኖች ጦርነቱን አቁመው መነጋገር መጀመር እንዳለባቸውም ጠቅሰዋል። የትግራይ ኃይሎች ግስጋሴያቸውን አቁመው ወደ ትግራይ እንዲመለሱም ጠይቀዋል። የተጣለው የሰብዓዊ እገዳ እንዲነሳ ብሄርን መሰረት ያደረገ ልዩነትና ከጥላቻ ትርክቶች መቆጠብም እንደሚገባ አሳስበዋል።


#አሜሪካ

በፀጥታው ምክር ቤት የአሜሪካ ተወካይ የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ባሳላፍነው አርብ ምክር ቤቱ ሁለቱም ተዋጊ ኃይሎች ከአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ወኪል ጋር እንዲተባበር የያዘውን አቋም ደግፈዋል።

ሊንዳ አንድ ዓመት ባስቆጠረው በዚህ ጦርነት ወቅት "ለረጅም ጊዜ በዝምታ ቆይተናል" ብለዋል። በጦርነቱ ወቅት መጠነ ሰፊ ሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸማቸውን የተናገሩት ሊንዳ፣ ይህም መድፈርን እንደ የጦርነት መሳሪያ መጠቀምን ያጠቃለለ ነው ብለዋል።

"ሁሉም ኃሃይሎች ጥፋተኞች ናቸው፤ ጥፋት የለሌለበት የለም" ሲሉ አምባሳደሯ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ለአንድ ወገን ያዳላል በሚል የሚቀርበበት ክስ አግባብ እንዳልሆነ ያጣጣሉት ሊንዳ ተቋሙ ማንኛውንም ጥቃቶችን እንዲሁም በየትኛውም ወግን የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንደሚቃወም ተናግረዋል።

ሊንዳ የህወሓት ተዋጊዎች ጥቃታቸውን ወደ አዲስ አበባ እንዳያሰፉ እና አሁን ከአማራ እና አፋር አካባቢዎች በመልቀቅ ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ አሳስበዋል። እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የጦርነት ሕጎችን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ሕጎችን እንዲያከብር ጠይቀዋል።

"በመጨረሻም ሰላምን ሊያመጡ የሚችሉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው" ሲሉ አምባሳደሯ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

SOURCE : #UNSC #BBC

@tikvahethiopia

Report Page