UNSC

UNSC


ሀገራት በፀጥታው ም/ቤት ምን አሉ ?

#Russia

በተመድ ፀጥታ ም/ቤት የሩሲያ ተወካይ የኢትዮጵያ መንግስት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ያወጀው የተናጥል የተኩስ አቁም በህወሓት ሀይሎች መጣሱ አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የህወሓት ሀይሎች ከትግራይ ክልል ውጪ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ጥቃት መክፈታውን፤ የሀገር ውስጥ ፈናቃዮች ቁጥር በእጥፍ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።

“የሰብአዊ ድጋፍ ጉዳይን ፖለቲካዊ ማድረግ ተገቢ አይደለም፣ በሚዲያ የሚካሄደው መርዛማ አካሄድ የመሳካት እድሉ አነስተኛ ነው” ብለዋል፤ ሰብአዊ ድጋፍ ሲቀርቡ ለትግራይ ብቻ ተብሎ ሳይሆን፤ ለአማራ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ኦሮሚያም ክልሎችም መሆን አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

“በኢትዮጵየ ፖለቲካው ውይይት እንደጀመር እንደግፋለን፤ ነገር ግን ውይይቱ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት #በኢትዮጵያውያን መሪነት ሊካሄድ ይገባል”ም ብለዋል።

ለኢትዮጵያ የሚረጉ ድጋፎች የሀገሪቱን ሉአላዊነት እና አንድነት ባስጠበቀ መልኩ ሊካሄድ ይገባል ያሉ ሲሆን፤ በሰኔ ወር በተካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያን የመረጡት መንግስት ሀገሪቱን ወደ ቀድሞ መስመር የመመለስ አቅም እንዳለው የሩሲያ መንግስት ያምናል ሲሉ ተግረዋል።

#China

የቻይና ተወካይ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም አካላት በራሳቸው መንግድ በሚያድርጉት የፖለቲካ ውይይት ልዩነቶቻቸውን እንደሚፈቱ ቻይና ታምለች ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ስራቸውን በሚሰሩበት ጊዜ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ መሆን ይገባል ብለዋል።

ለኢትዮጵያ የሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በሰብአዊ መብት እና በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በኢትዮጵየ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶችን ቻይና አጥብቃ ትቃወማለች ብለዋል።


#KENYA & #INDIA

የኬንያ እና የህንድ ተወካዮችም የትግራይ ክልል ግጭት መፍትሄ በኢትዮጵየውያን መሪነት መምጣት አለበት የሚል ሀሳብ አንስተዋል።

ክካኬንያ


#France & #Ireland

የፈረንሳይ እና አየር ላንድ ተወካዮች በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፈጠሩ ነገሮች አሳሳቢ ናቸው ያሉ ሲሆን፤ የህወሓት ሀይሎች በአስቸኳይ ከወረሩት የአፋር እና የአማራ ክልል ለቀው እንዲወጡ፤ የአማራ ክልል ሀይሎች ከያዙት የትግራይ ክልል መሬት እንዲለቁ እንዲሁም ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል።


#USA

የአሜሪካ ተወካይ በአፋጣኝ ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ መስመር እንዲከፈት እና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያካተተ ውይይት እንዲጀመር አሜሪካ ጥሪ አቅርባ ነበረ፤ እስካሁ የተጀመረ ነገር የለም፤ በኢትዮጵያ መንግስተ በኩልም በጎ ምለሽ አላገኘንም ብለዋል።

የህወሓት ሀይሎች ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ገብተው በከፈቱት ጥቃት በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን በመጥቀስ፤ ይህ በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል ያሉ ሲሆን፤ “የኤርትራ ጦር በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ነው፤ አሁን ያለው የጦርነት እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ነው፤ ይህም አሜሪካን ያሳስባታል” ብለዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ ሚሊየኖች ለምግብ ችግር መጋለጣቸውን እና አሁን ባለው ሁኔታ በትግራይ ክልል ያሉ መጋዝኖች ውስጥ ክምችም ማለቁን በመጥቀስ፤ ለዚህም የኢትዮጵያን መንግስት ተወቃሽ አድርገዋል።

የህወሓት ሀይሎች የኤርትራ ስደተኞችን እያጠቁ ነው ያሉት ተወካዩ፤ “አንድ የሰብአው ድርጅት ሰራተኛም በህወሓት ሀይሎች ተገድሏል፤ በርካታ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ንብረቶችም በእነዚሁ ሀይሎች ተዘርፈዋል” ብለዋል።

“ወታደራዊ መፍትሄ የለም፤ በአፋጣኝ ወደ ተኩስ አቁም ይገባ” ያሉት ተወካዩ፤ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉም ሀይሎች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመክሩ እና ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት እንዲጀመርም ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia

Report Page