Tx sl cmp fr vi ins bu gn ot የማቻከል ወረዳ ገንዘ

Tx sl cmp fr vi ins bu gn ot የማቻከል ወረዳ ገንዘ

Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጐጃም ዞን የማቻከል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በወረዳው ዉስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች ፡-ማለትም

  • 1 የሰራተኛ ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ
  • 2.የሰራተኛ የደንብ ጫማ
  • 3.የሰራተኛ ደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች
  • 4.የኤሌክትሪክ እቃዎች
  • 5.ኮምፒዉተርና ተዛማጅ ዕቃዎች
  • 6.የምስልና ድምጽ መቅረጫ ዕቃዎች.
  • 7.የጽህፈት መሳሪያ
  • 8.የፅዳት እቃዎች
  • 9.የዉጭ ፈርኒቸር
  • 10.የሃገር ዉስጥ ፈርኒቸር
  • 11.የተሸከርካሪ መኪና መለዋወጫ እቃዎች
  • 12.የመኪና ጥገና
  • 13.የስፖርት ትጥቅ አልባሳት
  • 14.ቶርሽን ጫማ
  • 15. ሲሚንቶ
  • 16.አሸዋ
  • 17.ጀኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛትና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ
  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በማቻ/ወ/ገ ኢ/ት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን የዕቃዉን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ ሞልቶ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን አድራሻ ህጋዊ ማህተም ሙሉ ስምና ፊርማ በመፃፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም በዋጋ መሙያዉ ላይ ስርዝ ድልዝ በግልጽ የማይነበብ በፍሉድ የጠፋ የጨረታ ሰነድ ያቀረበ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  4. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት ዋጋ ከ200‚000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር/በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ተራ ቁጥር 3,4,6,8,13,14,17 ብር2,000.00/ሁለት ሽህ ብር/ እና ተራ ቁጥር 5 እና 7 ብር 10,000.00/አስር ሽህ ብር/ ሲሆን ለሌሎች ግን ብር 5,000.00/አምስት ሽህ ብር/ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ/ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/unconditional Bank Guarantee/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ውድድሩ በምድብ ሎት በጥቅል ድምር ዋጋ የእያንዳንዱ ሎት አሸናፊ የሚለይ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል አንዱንም እቃ ሳይሞላ ቢቀር ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  7. መ/ቤቱ በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር 20 ከፍ ወይም ዝቅ የማለት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው አይነትና ስፔስፊኬሽን መሰረት በትክክል ተሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፉበትን እቃ ከተማው ውስጥ ባሉት ሴ/መ/ቤቶች ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች ለሚፈጥሩት ስህተት ለሚደርሰዉ የጉልበትም ሆነ የገንዘብ ኪሳራ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  11. ጨረታዉ በ16ኛ ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጐ ከጥዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡በዚሁ እለት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጐ ከጥዋቱ በ4፡00 ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
  12. ተጫራቾች ለደንብ ልብሶች ጽ/ቤቱ ያቀረበዉን ናሙና ማየት የሚኖርበት ሲሆን አሸናፊው ድርጅትም ለሁሉም የደንብ ልብሶች በናሙናዉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 777 00 480 ደውለው መረጃ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የማቻከል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ16ኛ ቀን ከጥዋቱ 3፡30


© walia tender

Report Page