Tx sl የደባይ ጥላት ግን ወ
Walia Tenderግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ጐጃም ዞን ገ/ኢ/ል/መምሪያ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ የስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የስፖርት አልባሣት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን፡-
- ከላይ በተጠቀሰው የስፖርት አልባሣት የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግበር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎች ማያያዝ እንዲሁም የግዥው መጠን 200 ሺህ ብር በላይ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ 30 ብር በመክፈል ከደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት ዋና ገንዘብ ያዥ ሰነዱን መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ በጥሬ ገንዘብ/በሲፒኦ/ ለሚወዳደሩበት የስፖርት አልባሣት 1,500 ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ጥ/ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ዘወትር በሰራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ጥ/ግን/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጐ በ3፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በጥቅል ዋጋ ዝቅተኛ የሰጠ መሆኑ ታውቆ ለሁሉም እቃዎች ዋጋ መሞላት ይኖርበታል፡፡
- እቃዎች ገቢ ሲሆኑ በተዘጋጀው የስራ ዝርዝር መሰረት በባለሙያ ተረጋግጦ ገቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በበዓላት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች እቃዎችን በደ/ጥ/ግን/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስር ባሉ ንብረት ክፍሎች ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 2570143 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 2570257/035 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ካሸነፈ በኋላ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ለውል ማስከበሪያ ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
የደባይ ጥላት ግን ወረዳ የስፖርት ጽ/ቤት
Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013
Deadline:በ16ኛው ቀን 3፡00
© walia tender