Tx pr sl fr የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ
Walia Tenderግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2013 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሥራ ሂደቶች አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎችን ለመግዛት
- ሎት 1 የተዘጋጀ የደንብ ልብስ ፣
- ሎት 2 ጫማ፣
- ሎት 3 የህትመት ዉጤቶች፣
- ሎት 4 የፅህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 5 የጽዳት እቃወች፣
- ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና
- ሎት 7 የፈርኒቸር እቃዎች ለመግዛት መስፈርቱን አሟልተዉ ከሚገኙ
አቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ሴት ታክስ /ቫት/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙት የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ከተጠቀሰው ስፔስፌኬሽን ውጭ ሰርዞ ሌላ ስፔስፌኬሽን መቀየር ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20 (ሃያ )ብር በመክፈል በማዕ/ጎ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ድምር ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከመ/ቤታችን የግዥና ን/አስ/ቡድን ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ 1 ለማስያዙ የገቢ ደረሰኝ
- አስቆርጦ ከሚወዳደርበት ሰነድ ጋር የደረሠኙን ኮፒ በማሸግ ማስገባት አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት ሲፒኦ ከ1 በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማዕ/ጎ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ ጸንቶ የሚቆይበት ከመስከረም 25/2012 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 09/2012 ዓ/ም ድረስ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማዕ/ጎ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ጥቅምት 10/2012 ዓ/ም ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በቀኑና በሰዓቱ ካልተገኙ ጨረታዉን ከመክፈት አያግድም፡፡
- አሸናፊው እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል እና የርክክብ ቦታ ሰ/ጎ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ን/ክፍል ይሆናል፡፡
- ተጫራቾቸ በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በነጠላ በሞላው ዋጋ ሲሆን ተጫራቾች ሁሉንም ዝርዝር ዋጋ መሙላት አለባቸው ፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም
- አሸናፊው ተጫራች የእቃዎችን ጥራት በተመለከተ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጥራቱን በማረጋገጥ ማስረከብ ግዴታው ነው፡፡ በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ መሰረት የጥራት ችግር ያለባቸውን ሙሉ በሙሉ በመመለስ ትክክለኛ ጥራት ያላቸውን እቃዎች የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ይህን ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 0584174941 ደዉለዉ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም መስከረም 25/2012 የወጣውን በኩር ጋዜጣ መመልከት ይችላሉ፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013
Deadline:ጥቅምት 10/2012
© walia tender