TX SL CMP BU VI AG የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል

TX SL CMP BU VI AG የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል


Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በይልማና ዴንሣ ወረዳ የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን

  • ሎት 1 ብትን የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችና ጫማዎች፣
  • ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ/ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣
  • ሎት 4 የማዳበሪያ ጆንያ ለማሰራት፣
  • ሎት 5 የህንፃ መሣሪያዎች፣
  • ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ፣
  • ሎት 7 የፅህፈት መሣሪያዎች፣
  • ሎት 8 የግብርና እቃዎች፣
  • ሎት 9 የፅዳት እቃዎች እና
  • ሎት 10 የመኪና ጎማዎችና ካላማደሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ሰነዶችን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና አስፈላጊ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6.  የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 20 በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 27 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/በሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡30 በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ስም አድራሻ የሚመለከተው/ህጋዊ ወኪል/ የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ተጫራቾች በዘርፉ እንዲወዳደሩ የሚያስችል ንግድ ፈቃድ ካላቸው ከአንድ በላይ ሎት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ዋስትና 10 በመቶ በሲፒኦ በማስያዝ ውል መፈፀም ያለባቸው ሲሆን ተጫራቹ አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ማዕከሉ ድረስ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  14. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 26 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 3381166 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል

__________________

Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00

__________________
© walia tender

Report Page