Sl vi mt tx bu ag lb md fr ot የጓንጓ ወረዳ ገ/ኢ
Walia Tenderግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገ/ኢ/ትብ/ቢሮ የአዊ/ብሔ/አስ/ገ/ኢ/ትብ/ ዋና መምሪያ የጓንጓ ወረዳ ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳድር ቡድን
ለ2013 በጀት አመት
- ሎት 1 ስቴሽነሪ
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 3 የፅዳት ዕቃ
- ሎት 4 የመኪና ጐማ እና የሞተር ሳይክል ጐማ
- ሎት 5 የስፖርት አልባስት
- ሎት 6 የተዘጋጁ ልብሶች
- ሎት 7 ብትን ጨርቅ
- ሎት 8 ደንብ ጫማ
- ሎት 9 የህንፃ መሳረያ
- ሎት 10 የመኪና ስፔር ፓርት
- ሎት 11 አፍሬዴቭ ፓንፕ
- ሎት 12 የስፖርት ቁሳቁስ
- ሎት 13 ክሎሪን
- ሎት 14 የአገር ውስጥ ፈርኒቸር
- ሎት 15 የእንስሳት መድሃኒት እና ቁሳቁስ
- ሎት 16 የውጭ ፈርኒቸር ግዥ አወዳድሮ መግዛት
ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል ::
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችል፣
- የሚገዛዉ የግዥ መጠን ከ200‚000.00 ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባችዋል፣ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የንግድ ፈቃድ ቲን ሰርተፊኬትና ቫት ሰርተፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ዉስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በበኩር ጋዜጣ (በግልፅ ጨረታ) ከወጣበት ከ 25/01/2013ዓ.ም ጀምሮ 09/02/2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱ ጓ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት የግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 የማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ ብር ብቻ/ መግዛት ይችላሉ::
- የማወዳደሪያ ስርዓቱ የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ነው::
- የሁሉም ጨረታ ሰነድ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፌኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላሉ::
- ተጫራቾች የጫራታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ /መሂ-1/ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ::
- ማንኛዉም ተጫራቾች የጫራታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ጓ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት እለት ከ 25/01/2013ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 10/02/2013ዓ.ም እስከ 4፡00 የመጫረቻ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል ::
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በጓ/ወ ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ16ኛዉ ቀን የጨራታ ሳጥኑ ከጥዋቱ 4፡00 ስዓት ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል:: ነገር ግን 16ኛዉ ቀን ወይም የሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል::ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈዉ ዉሳኔ ተገዥ ይሆናሉ::
- ተጫራቾች ንግድ ፍቃዳቸዉ በሚጋብዛቸዉ ብቻ መወዳደር አለባቸው::
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በጓ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት በራሳቸዉ ወጪ በማምጣት በባለሙያና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች በማስፈተሸ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መሙላት የተከለከለ ነዉ ::
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የንግድ ፈቃድ፣ ቲን፣ቫት እንዲሁም ያሚሞላቸው ሰነዶች ለሦስተኛ ወገን በግልፅ የሚታይና የሚነበብ መሆን አለበት::
- ማንኛዉም ተጫራች በሚያቀርበው መወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን ፤ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው::
- መ/ቤቱ የግዥውን መጠን 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብት አለው::
- የሞሉት ዋጋ ማንኛውም ወጪ በራሱ መሽፈን አለበት::
- ተጫራቾች በግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን አለባቸው::
- የሞሉት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ቀን ፀንቶ ይቆያል::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጫራታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582250506 ፣ 0582250009 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ::
የጓንጓ ወረዳ ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት
Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013
Deadline:በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
© walia tender