Sl tx pr vi ot በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አ

Sl tx pr vi ot በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አ

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡001/2013

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2013 በጀት አመት የሚያስፈልጉትን

ሎት 1:-የፅህፈት መሳሪያዎች፣
ሎት 2፡- የፅዳት እቃዎች፣
ሎት 3፡- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
ሎት 4፡- የደንብ ልብስ፣
ሎት 5፡- ህትመት፣
ሎት 6፡- የመኪና ጎማ፣

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. ለሎት 1 :-2000 ብር ; ለሎት 2፡- 3000 ብር : ለሎት 3፡2500 ብር : ለሎት 4 ፡-3000 ብር፣ ሎት 5፡ 1500 ብር እና ለሎት 6፡- 2000 ብር በባንክ በተረጋገጠ CP0 ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የቫት እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበትእለትጀምሮለ10ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከል/ክ/ከ/ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት1፣ሎት2፣ሎት3፣ ሎት 4 እና ሎት5 ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
  6. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው እቃዎች በእያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ ላይ ቫት ጨምረው የግድ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እቃውን በራሱ ትራንስፖርት በሰጠው ናሙና መሰረት ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  9. የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በአስረኛው(10ኛው) ቀን በ9:00 ሰአት ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 9፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሸጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወ/2/ፋ/ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡
  10. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለበለጠ መረጃ ፡- ጦር ኃይሎች ወደ 18 በሚወስደው መንገድ 700 ሜ ገባ ብሎ ኪዳኔ ገብሬ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ስልክ ቁጥር፡- 01137133-24 /011-371-33-21

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ2

አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 8፣2013

Deadline: በ10ኛው ቀን 9፡00


© walia tender

Report Page