Sl tx fr vi የመካነ ኢየሱስ/ከ/አስ/ገን/አ

Sl tx fr vi የመካነ ኢየሱስ/ከ/አስ/ገን/አ

Walia Tender

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ጎንደር ዞን የመካነ ኢየሱስ/ከ/አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣
  • ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 3 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች፣
  • ሎት 4 የተዘጋጁ ጫማዎች፣
  • ሎት 5 የኤሌክትሪክ አቃዎች፣
  • ሎት 6 የስፖርት እቃዎች፣
  • ሎት 7 ፈርኒቸር /የቤት እና የቢሮ እቃዎች/ የዉጭ እና የሃገር ዉስጥ፣
  • ሎት 8 የመኪና ጎማ፣
  • ሎት 9 ብትን ጨርቅ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የገንዘብ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ሰትርቲፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከመ/ኢ/ከ/አስ/ገ/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የእቃውን ዝርዝር መግለጫዎች /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ሎት 3፣ ሎት 4 እና ሎት 9 ወይም ብትን ጨርቅ፣ የተዘጋጁ ጫማዎች ፣የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች በሚቀርበው ናሙና ከተቋማችን ላይ ይገኛል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደርበት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ማንኘውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ ላይ እና ፖስታው ላይ የንግድ ድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለበት፡፡
  11. 1ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን ባንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅች ማለትም ዋና ና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ መ/ኢ/ከ/አስ/ገ/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  12. ጨረታው በ 16ኛው ቀን ሎት 1 ፣ 2፣3 እና 4 ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡15 ይከፈታል፣ ሎት 7 ፣8 እና 9 ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 7፡30 ይከፈታል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ እስከሚዘጋበት ስዓት ድረስ ጨረታው ማስገባት ይችላል፡፡ ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈትይሆናል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች በዝርዝር ወይም በሎት ከቀረቡት እቃዎች ውስጥ ዋጋውን ነጥሎ መሙላት አይችልም፡፡ ነጥሎ የሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  15. የጨረታ አሸናፊው እንደተቋሙ ፍላጎት በጥቅል ወይም በተናጠል ሊለይ ይችላል፡፡
  16. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ በሙሉ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ከገዥው ተቋም ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  17. አሸናፊ ከሆነው ተጫራች ላይ 2 በመቶ ከተከፋይ ሂሳብ ግብር /With holding TAX/ ተቀናሽ ይሆናል፡፡
  18. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውሉን መፈጸም ይኖረበታል፡፡ በተባለው ቀን መጥቶ ውሉን የማይፈፅም ከሆነ ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  19. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  20. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0584470121 እና 0584471022 በመደወል ማግኘትይችላሉ፡፡

የመካነ ኢየሱስ ገንዝብ አካባቢ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በሎት የተለያየ ነው


© walia tender

Report Page