Sl tx fr mt የምስራቅ በለሣ ወ/ገ/ኢ
Walia Tenderግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ በለሣ ወ/ገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት በምስ/በ/ወረዳ ስር ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎትየሚውል በመደበኛ በጀት የሚገዙ በምድብ የተገለፁትን
- በምድብ 01 የስቴሽነሪ እቃዎች፣
- በምድብ 02 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- በምድብ 03 የደንብ ልብስ እቃዎች፣
- በምድብ 04 የፈርኒቸር እቃዎች እና
- በምድብ 05 የሞተር ሣይክል ስፔር ፓርት እቃዎችን በየምድባቸው በጋዜጣ በወጣው ግልጽጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መወዳደር ለምትፈልጉ ድርጅቶች በሙሉ የጨረታሰነዱን በምስ/በ/ወ/ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 በግንባር በመቅረብ የማይመለስ 80 ብር በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለመጫረት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፊኬት/ቲን/ ማቅረብየሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን 1 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው የሚገቡትን ውለታ በአግባቡ የሚፈጽሙ መሆን አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌላ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶችን በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበትቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት የምትችሉመሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው ለ15 ቀን አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት 3፡00 ሁሉም ጨረታዎች ተዘግተው ከ3፡30 ጀምሮ እንደ የምድባቸው ቅደምተከተል በይፋ ይከፈታል፡፡
- የታዘዙት እቃዎች በበጀት እጥረት ምክንያት ሣይገዛ ቢቀር የማንገደድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የበዓላት/ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የቅሬታ ቀን ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5/አምስት/ የስራ ቀናትማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- . አሸናፊ የሚለየው በሞሉት ዝቅተኛ በጥቅል ድምር ዋጋ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ ምስ/በ/ወ/ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 በአካልበመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 3390116 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ድርጅቱ ከፖስታው ላይ ማህተሙን ፣ ስምና ፊርማውን ማስቀመጥ አለበት፡፡ የሚቀርቡትእቃዎች በስፔስፊኬሽንኑ መሰረት ኦርጅናል መሆን አለባቸው፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች እስከ ምስ/በ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች መጋዘን ድረስ ማድረስ የሚችልእንዲሁም መጫኛና ማውረጃ በነጋዴው የሚሸፈን መሆን አለበት፡፡
የምስራቅ በለሣ ወ/ገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት
Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013
Deadline:በ16ኛው ቀን 3፡00
© walia tender