Sl pr tx fr የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት

Sl pr tx fr የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት

Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገ/ኢ/ል/ቢሮ የሰ/ወሎ ዞን መምሪያ የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎትየሚውሉ የተለያዩ እቃዎች አቅርቦት

የህትመት አቅርቦት ግዥ

ሎት 2

የጽህፈት መሣሪያ አቅርቦት ግዥ

ሎት 3

የኤሌክትሮኒክስ አቅርቦት ግዥ

ሎት 4

የጽዳት እቃዎች አቅርቦት ግዥ

ሎት 5

የተዘጋጁ ደምብ ልብሶች አቅርቦት ግዥ

ሎት 6

የተዘጋጁ ደንብ ጫማዎች አቅርቦት ግዥ

ሎት 6

የተዘጋጀ ጣቃ ጨርቅ ወይም ብትን ጨርቅ አቅርቦት ግዥ

ሎት 7

ያልተዘጋጀ ጣቃ ጨርቅ ወይም ብትን ጨርቅ አቅርቦት ግዥ

ሎት 8

ቋሚ የቢሮ እቃዎች አቅርቦት ግዥ

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችመወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሰረት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸውና የሚሞሉት ዋጋ 200ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር ለህትመት እና ለጽ/መሣሪያ፣ 30 ብር ፣ ለሌክትሮኒክስ 20 ብር እናለቋሚ የቢሮ እቃዎች 25 ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን የተዘጋጁ የደንብ ጫማዎች እና የተዘጋጁ ደምብ ልብሶች እናያልተዘጋጁ ጣቃ 15 ብር ብቻ እና የጽዳት እቃዎች 10 ብር በመክፈል ላስታ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት የሞሉትን ዋጋ 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከባንክበተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ጨረታ ከመከፈቱ በፊትበጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖበታል፡፡
  4. ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሁኖ ይቆይናበ16ኛዉ ቀን ጠዋት 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. የተጠቀሰዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይተላለፍ እና ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በላስታ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን በየሎት ምድባቸው በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ከላይበተጠቀሰዉ ቀንና ሰአት ዉስጥ ላስታ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  7. አሸናፊዉ አካል እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ሲኖርበት ንብረቱን ገቢ የሚደረገዉበባለሙያ እየተረጋገጠ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታራሳቸዉን ማግለል አይችሉም ፡፡
  9. ተጫራቾች በአንድ ሎት ዉስጥ የተዘረዘሩትን የዕቃ አይነቶች ከፍሎ መሙላት አይቻልም ዉድድሩ የሚካሄደው በየሎት ድቡ ጥቅልብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለበት ፡፡
  10. የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  11. የተዘጋጁ እና ላልተዘጋጁ የደንምብ ልብሶች እና ደንምብ ጫማ ለሚወዳደሩ አቅራቢዎች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  12. ፍ/ቤቱ የጨረታዉን ዉጤት በማየት ከበጀቱ ጋር ለማጣጣም 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመ/ቤታችን

ስልክ ቁጥር 0333361187 ወይም 0921964766 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ16ኛዉ ቀን ጠዋት 4፡00


© walia tender

Report Page