Sl md vi tx bu fr የጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ፋ

Sl md vi tx bu fr የጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ፋ

Walia Tender

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል

  • ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ፅህፈት መሣሪያ፣
  • የእንስሳት መድኃኒት እና አላቂ ህክምና ዕቃዎች፣
  • የመኪና ጎማ እና ከመነዳሪ፤
  • የሞተር ጎማ እና ከመነዳሪ፤
  • የደንብ ልብስ፤
  • የደን ዘር፤
  • የፅዳት ዕቃ፤
  • የሕንፃ መሣሪያ፤
  • ፈርኒቸር
  • ሞተር ሳይከል ካዝና እና ምድር ሚዛን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ፡-

  1. ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑግብር የከፈሉና ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ እና ህጋዊ ማስረጃቸውንና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. 3ተጫራቾች የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
  4. የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. በጨረታ ሰነዱ የተዘረዘሩ ዕቃዎች ዝርዝር በሙሉ አቅም የሚያቀርቡ ሆኖ ለየትኛውም አይነት ዕቃ ናሙና ሲጠየቁ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኤሌከትሮኒክ፤ የጽሕፈት መሣሪያ፤ ሞተር ሳይክል ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለመኪና ጎማ ፣ ለሞተር ጎማ እና ከመነዳሪ፤ የህንፃ መሣሪያ፤ ፈርኒቸር፤ ካዝና እና ምድር ሚዛን ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ለእያንዳንዳቸው ለእንስሳት መድኃኒት እና አላቂ የህክምና ዕቃዎች የደንብ ልብስ፤ የደን ዘር፤ የፅዳት ዕቃ ብር 2,000(ሁለት ሺህ ብር) ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በእንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ከግ/ን/አስ/ስ/ሂደት ለእያንዳንዳቸውየማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር)ከፍለው የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ዘወትር ከሰኞ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት በመቅረብ በዋጋ ማቅረቢያችሁ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒውን በመ/ቤታችን ስም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ዕለት በ9፡30 ሰዓት ላይ በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ወይም በሚመቻች ከፍል ይከፈታል፡፡
  9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ ድርጅት ዕቃውን የሚያስረከበው እንደጋኝ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ንብረት ከፍል ገቢ በማደረግ ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 011 350 00 47/46

በጉራጌ ዞን የእንደጋኝ ወረዳ

ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

/ድንቁላ/


Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 11፣2013

Deadline:በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30


© walia tender

Report Page