Sl bu ot ins የባህር ዳር መንገዶች ባለ
Walia Tenderግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት የመብራት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፣
- የግብር ከፋይ መለያ/ቲን/ ያላቸው፣
- በስሙ የታተመ ማህተምና ደረሰኝ ያለዉ፣
- የግዥው መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ(ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1--3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ናሙና የቀረበ ስለሆነ የጨረታ ሰነዱን ሲወስዱ ማየት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ 50,000 ሀምሳ ሽህ/ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ከ25/01/2013 ዓ/ም እስከ 10/02/2013 ዓ/ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ10/03/2013 ዓ/ም ቀን 8፡30 ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊዉ የሚለየዉ ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበ ይሆናል
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ኦርጅናል ዕቃ በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማጓጓዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባ/ዳር ከ/አስ/ መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብረት አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-320-324-6 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት
Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013
Deadline:10/03/2013
© walia tender