Sl አንፕካን

Sl አንፕካን

Walia Tender

በድጋሜ የወጣ የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ አልትራ ሬድ ( የሙቀትመለኪያ መሳሪያ) ጓንት ሳኒታይዘር፣ አልኮል፣ የእጅ መታጠቢያ ፈሳሽሳሙና እና የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ግዢ ጨረታ

አፍሪካን ኔትወርክ ፎር ዘ ፕሪቬንሽን ኤንድ ፕሮቴክሽን አጌይንስት ቻይልድ አቢዩዝኤንድ ኔግሌክ (አንፕካን) - ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆንከፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትበአዊ ማሀበረሰብ ዞን በሚገኙ 3 ወረዳዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትንና በወረዳዎችየሚገኙ የፕሮጀክት ተጠቃሚዎችን ተጋለጭነት ለመቀነስ ይረዳ ዘንድ የአፍንጫናአፍ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ አልትራ ሬድ (የሙቀት መለኪያመሳሪያ)፣ጓንት፣ሳኒታይዘር፣ አልኮል፣ የእጅ መታጠቢያ ፈሳሽ ሳሙና፣ እና የሴቶችየንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡

  1. በዘርፎቹ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO)ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
  3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
  4. ተጫራቾች የግዥውን ዝርዝር ሰነድ አዲስ አበባ፤ የካ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 09፤ ጉርድሾላ፤ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አጠገብ በሚገኘዉ 10 እህትማማች ድርጀቶች ህንፃ 4ኛፎቅ ላይ በሚገኘዉ የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት መዉሰድ ይችላK::
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእጅ መታጠቢያ ፈሳሽ ሳሙና፣ ሳኒታይዘርና አልኮልናሙናዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚጠበቅባቸዉ ሲሆን፤ ካሸነፉምበተወዳደሩበት ሳምፕል መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  6. የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን (ማስክ) በተመለከተ ተጫራቾች ድርጅቱባዘጋጀዉ ናሙና መሰረት ብቻ መወዳደርና ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  7. የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ አልትራ ሬድ (የሙቀት መለኪያ መሳሪያ) እናጓንት ማቅረብ የሚችሉት በዘርፉ ፈቃድ ያላቸዉና ከኢትዮጵያ ምግብ፣ መድሃኒትናጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብየሚችሉ ብቻ ናቸው::
  8. የጨረታ አሽናፋዎች የሸነፉበትን እቃ ወዲያውኑ ማስረከብ የሚችሉ መሆንይኖርባቸዋል::
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታበመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግና ሁለቱን ፖስታዎችበአንድነት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀንአንስቶ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባትይችላሉ::
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8 ኛው ቀንከጠዋቱ በ4 ፡00 ታሽጎ በ4 ፡30 ሰዓት ይከፈታል::
  11. ተጨራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱየተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በአንል ደውለው መጠየቅይችላሉ::

አንፕካን ኢትዮጵያ፤ የካ ክ/ ከተማ፤ ወረዳ 09 ጉርድ ሾላ፣

አትሌቲክስ ፌደሬሽን አጠገብ በሚገኘዉ 10 እህትማማች ድርጀቶች ህንፃ፤4 ፎቅ

ስልክ 011-5505202 /011-5502222

አንፕካን - ኢትዮጵያ


Posted:ሪፖርተር ነሀሴ 6 ቀን 2012
Deadline: August 19, 2020


© walia tender

Report Page