#Shire 

#Shire 


የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰኞ ምሽት በትግራይ ሽረ ከተማ ተፈናቃዮች ከሚገኙበት አራት ካምፖች ከ500 በላይ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በግዳጅ ይዘው መውሰዳቸውን 3 የእርዳታ ሰራተኞችና አንድ ዶ/ር እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል።

የእርዳታ ሰራተኞቹ እና ዶክተሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኪናዎች ላይ ተጭነው ተወስደዋል ሲሉ ፤ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል።

ከእርዳታ ሠራተኞች መካከል አንዱ እንዳሉት በርካታ ወንዶች ተደብድበዋል ፣ ስልካቸው እና ገንዘባቸው ተወስዷል።

በአንዱ ካምፕ ውስጥ የሚኖርና ክስተቱ በተፈፀመበት ወቅት የተደበቀ አንድ ግለሠብ ወታደሮች ሰብረው ገብተው ሰዎችን በዱላ መደብደባቸው ተናግሯል።

ይኸው ስሙ በሚስጥር እንዲያዝ የጠየቀው ግለሰብ፥ ወታደሮች በምሽት መጥተው ካምፑን በመክበብ ዋናውን በር በመስበር ያገኙትን ሁሉ በዱላ መደብደብ እንደጀመሩ ገልጾ በወቅቱ የ70 ዓመት አዛውንት መደብደባቸውን እና አንድ አይነስውር አፍነው መውሰዳቸውን ተናግሯል።

እሱ ካለበት "ፀሃዬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት" ብቻ 400 ሰዎች መወሰዳቸውን አስረድቷል።

የመከላከያ ቃል አቀባይ፣ የትግራይ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡበት መልዕክት ቢቀመጥላቸውም ምላሽ አልሰጡም ብሏል ሮይተርስ።

የሰሜን ምዕራብ ዞን ጊዜያዊ ኃላፊ ቴዎድሮስ አረጋይ ጥቂት መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ክሱን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፕሮፖጋንዳ ነው ብለውታል።

ማክሰኞ ጥዋት ቤተሰቦቻቸው የተወሰዱባቸው በርካታ ሰዎች በተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ ቢሮ ፊት ለፊት ሰልፍ ስለማድረጋቸው ሮይተርስ በደረሰኝ ምስሎች ተመልክቻለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia

Report Page