SL TX VI ደ/ታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

SL TX VI ደ/ታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ደቡብ ጐንደር አስ/ዞን የደብረታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለቢሮ መገልገያ እና ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ

ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፤
ሎት 2. ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች፤
ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፤
ሎት 4. የፅዳት እቃዎች
ሎት 5.የደንብ ልብስ
ሎት 6 የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግዥ መጠን 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነትን የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1.-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚነበቡ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  5.  የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00. /ሀምሳ ብር / በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 1.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ/1 በመቁረጥ ደረሰኙን ኮፒ አድርገው በጨረታ ፖስታው ውስጥ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በሁለት ቅጂዎች ማለትም ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በተለያየ በታሸገ ፖስታ በደ/ታ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አ/ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 1 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 በ16ኛው ቀን በ3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ የህዝብ በዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር 20,000 /ሀያ ሽህ ብር/ እና በላይ ሽያጭ ከተፈጸመ 7.5 በመቶ ቫት ይቀንሳል፡፡
  11. ተጫራቶች የሚወዳደሩበት በቫት ከሆነ የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰውን መለያ /ስፔስፊኬሽን/ መቀየር ወይም ስያሜ መስጠት ወይም የማስተካከል ስራ ከተሰራ እና ስርዝ ድልዝ ካደረጉት ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  13. ተጫራቾች ያሸነፉቸውን እቃዎች ከግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ድረስ በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  14.  አሸናፊው የሚለየው በጥቅል/በተናጠል ዋጋ ይሆናል፡፡
  15. አሸናፊው ድርጅት በአሸነፈበት ዕቃ የዋጋ ድምር 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቶች ላወጡት ዋጋ ኮሌጁ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  17.  ስለጨረታው ማብራሪያ መጠየቅ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመገኘት ወይም በስ-ቁጥር 0584410447 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

ደ/ታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

__________________

Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:16ኛው ቀን በ3፡00


__________________
© walia tender

Report Page