SL TX PR በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋ
Walia Tenderየጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ለ2013 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የሚያስፈልጋቸው
1. የጽህፈት መሳሪያዎችና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፤
2. ቶነሮች ፤
3. የጽዳት ዕቃዎች፤
4 የደንብ ልብሶች ፤
5. ብትን ጨርቆች ፤
6. የደንብ ልብስ ስፌት፤
7. ህትመት ፣ እና
8.የስፖርት ዕቃዎችን
አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የምትችሉ፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
- የዘመኑን ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ
- የአቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ /ከአቅራቢነት ያልተወገዱ መሆን አለባቸው
- ቫት/TOT የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO በሚያቀርቡት ገንዘብ ዋጋ ለጽህፈት መሳሪያዎችና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ብር 2200.00 ፣ ለቶነር ብር 1500.00፤ ለጽዳት ዕቃዎች ብር 3500.00፤ ለደንብ ልብሶች ብር 2500.00፤ ለብትን ጨርቆች ብር 2000.00፣ለደንብ ልብስ ስፌት ብር 1500.00፤ ለህትመት ብር 600.00 እና ለስፖርት ዕቃዎች ብር 500.00 ማቅረብ አለባቸው ፤
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) ለ አንድ ሎት መክፈል አለባቸው፣ ከአንድ ሎት በላይ የሚገዙ አቅራቢዎች ተጨማሪ በሚገዙት በያንዳዱ ሎት 50 ብር ለመክፈል ይገደዳሉ ፤
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዋና የስራ ሂደት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም በማሳረፍበታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአ/ከ/ክ/ከ/ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሉት ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፤
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም የቴክኒካል ሰነድ ለየብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ፤
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለበት በሙሉ መሞላት አለባቸው፤
- የጨረታ ሰነዱ እና የዋጋ ማቅረቢያው ሳይለወጥና ሳይቀነስ በሙሉ የማይመልስ አቅራቢ ከጨረታው ይሰረዛል ፤
- . ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ጀምሮ ሎት 1-2፤ በሚቀጥለው ቀን ሎት 3-4 እና በ3ኛው ቀን ከሎት 5-9 ያሉ የሚከፈቱበት ይሆናል፡፡
- በተራ ቁጥር 13 ላይ የተጠቀሰው በሎት የመከፋፈል ስራ ይመች ዘንድ ከአንድ ሎት በላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለብቻ ማሸግ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ 2 ቀን በፊት ለሁሉም ዕቃዎች ናሙና ወይም ስፔስፊኬሽን ወይም ፎቶ ወይም ማንኛውም ስለ ዕቃው የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ መቻል አለባቸው፤ የናሙና መቀበያ ቅጽ በ2 ኮፒ አዘጋጅቶ አብሮ ማቅረብ መቻል አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላዋጋ ከVAT TOT በፊት ያለ ስርዝ ድልዝ በትክክል መሞላት አለበት
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሱን ማግለል አይቻልም ፣
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡ ከአውቶቢስ ተራ ወደ አጣና ተራ በሚወስደው መንገድ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ ሠፈረ ሰላም ት/ቤት ፊት ለፊት በአ/ከክ/ከ/ወረዳ 4 አስተዳደር ህንጻ ምድር ላይ ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4
- ስልክ ቁጥር፡- 011-827-71-97 /011-827-6260
በአዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
__________________
Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 8፣2013
Deadline:በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
__________________
© walia tender